Loading
አዝ፦ ዓይኖቼ ፡ አይተውህ ፡ እጅጉን ፡ ፈዘዙ የፍቅርን ፡ እንባ ፡ አወጡ ፡ ከቶ ፡ ሳይታዘዙ ነፍሴም ፡ አልቻለችም ፡ መድሃኒቷን ፡ ስታይ ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ (፪x) በደሌ ፡ እንደሙታን ፡ አድንዞኝ ፡ ሳለሁ በኢየሱሴ ፡ በኩል ፡ ወደአብ ፡ ዘንድ ፡ ገባሁ በሥጋዬ ፡ ምኞት ፡ እየኖርኩኝ ፡ ሳለሁ ከፍቅሩ ፡ የተነሳ ፡ ፀጋውን ፡ አገኘሁ አዝ፦ ዓይኖቼ ፡ አይተውህ ፡ እጅጉን ፡ ፈዘዙ የፍቅርን ፡ እንባ ፡ አወጡ ፡ ከቶ ፡ ሳይታዘዙ ነፍሴም ፡ አልቻለችም ፡ መድሃኒቷን ፡ ስታይ ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ (፪x) ቸርነቱን ፡ ሊያሳይ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አስነሳኝ በላይኛው ፡ ስፍራ ፡ በቀኙ ፡ አስቀመጠኝ እንግዲህ ፡ አልመካም ፡ ከስራዬ ፡ አይደለም በእምነት ፡ የተገኘ ፡ ስጦታ ፡ ነው ፡ ይኸው አዝ፦ ዓይኖቼ ፡ አይተውህ ፡ እጅጉን ፡ ፈዘዙ የፍቅርን ፡ እንባ ፡ አወጡ ፡ ከቶ ፡ ሳይታዘዙ ነፍሴም ፡ አልቻለችም ፡ መድሃኒቷን ፡ ስታይ ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ (፪x) ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ አደንቅሃለሁ በአንተ ፡ ውብ ፡ ፍቅር ፡ ተነድፌያለሁኝ (፪x) አዝ፦ ዓይኖቼ ፡ አይተውህ ፡ እጅጉን ፡ ፈዘዙ የፍቅርን ፡ እንባ ፡ አወጡ ፡ ከቶ ፡ ሳይታዘዙ ነፍሴም ፡ አልቻለችም ፡ መድሃኒቷን ፡ ስታይ ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.