Loading
ጽዋ ፡ ሲሞላ ፡ ሰዓቱ ፡ ሲደርስ የጌታ ፡ ሞገስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ሲፈስ ከፍታውም ፡ ዝቅ ፡ ሸለቆውም ፡ ከፍ ካለ ፡ በኋላ ፡ ጌታ ፡ ይላል ፡ ከተፍ (፪x) አዝ፦ በራሱ ፡ ምሎ ፡ በገዛ ፡ ክንዱ ጣልቃ ፡ የሚገባ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ እርሱ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ቀን ፡ የሚቀጥረው ያልተጠበቀን ፡ ነገር ፡ የሚያደርገው (፪x) ገና ፡ ብዙ ፡ አለ ፡ በመዝገቡ (፪x) እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ መሆኑን ፡ አይቼ እጮሃለሁኝ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ የማላቀውን ፡ ነገር ፡ የሚያሳየኝ እንደእግዚአብሔር ፡ ኧረ ፡ የት ፡ ሊገኝ (፪x) አዝ፦ በራሱ ፡ ምሎ ፡ በገዛ ፡ ክንዱ ጣልቃ ፡ የሚገባ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ እርሱ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ቀን ፡ የሚቀጥረው ያልተጠበቀን ፡ ነገር ፡ የሚያደርገው (፪x) ገና ፡ ብዙ ፡ አለ ፡ በመዝገቡ (፪x) ጌታ ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ ነውና ስለቤቱ ፡ የሚቀና ቃል ፡ የገባውን ፡ ይፈጽማል ተስፋውንስ ፡ መቼ ፡ ያጥፋል (፫x) ገና ፡ ብዙ ፡ አለ ፡ በመዝገቡ (፪x) ገና ፡ ብዙ ፡ አለ (ብዙ ፡ አለ) ብዙ ፡ አለ ፡ (ብዙ ፡ አለ) ብዙ ፡ አለ ፡ በመዝገቡ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.