Loading
ሁሉንም ፡ ትቼ ፡ እሮጣለሁ ያለኝንም ፡ ሁሉ ፡ አጣዋለሁ የሚጠቅመኝንም ፡ እተዋለሁ ብቻ ፡ አንድ ፡ ነገር አንድ ፡ ነገር ፡ እሻለሁ እርሱንም ፡ አውቃለሁ ሁሉም ፡ ቀርቶብኝ ፡ ቢገኝልኝ የሱስ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ ፡ የናፈቀኝ በእርሱ ፡ ተገኝቼ ፡ እርሱንም ፡ አግኝቼ ሌላ ፡ መሻት ፡ የለኝ ፡ የምራበው የሱስ ፡ ዕንቁዬ ፡ ነው እርሱን ፡ ከማወቅ ፡ ጋር ፡ ምን ፡ ይወዳደራል ሁሉን ፡ እርግፍ ፡ አድርጐ ፡ አስትቶ ፡ ያስኬዳል ሽልማቴ ፡ ሌላ ፡ መች ፡ ለእኔ ፡ ሆነልኝ እርሱ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ እኔን ፡ የወደደኝ (፪x) ሽልማቴ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ሽልማቴ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ (፪x) ሆነህ ፡ ተገኝተሃል ፡ በእኔ ፡ ዘንድ ፡ አንደኛ ሁሉንም ፡ አስናቀኝ ፡ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ እረኛ ፡ (፪x) የከበረ ፡ የገነነ ፡ እኔ ፡ እምሻው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ (፲፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.