Loading
አምላኬ ፡ እድሌ ፡ ፈንታዬ ያለመለምከው ፡ ተስፋዬን መሞት ፡ ሲገባኝ ፡ ኩነኔ እኔስ ፡ ገረመኝ ፡ መዳኔ (፪x) ገረመኝ ፡ መዳኔ ፡ መዳኔ ፡ ገረመኝ ፡ መዳኔ (፪x) ውለታ ፡ ያለበት ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል ፍቅሩን ፡ የቀመሰ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል ያደረግልኝን ፡ ጌታ ፡ ይሆነልኝን አስቤው ፡ ያን ፡ ዘመን ፡ በርሱ ፡ ያለፍኩትን ክበር ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ ንገሥ ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ ክበር ፡ ልበለው ፡ አከብረዋለሁኝ ንገሥ ፡ ልበለው ፡ አነግሰዋለሁኝ ቅጥቅጥ ፡ ሸንበቆ ፡ አትሰብርም የወደቀ ፡ አይተህ ፡ አታልፍም አልቀረሁ ፡ ምስኪን ፡ ተብዬ ባንተ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ (፪x) ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ (፫x) ቃሉን ፡ ያሰበ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል ከሞት ፡ ያመለጠ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል ያደረግልኝን ፡ ጌታ ፡ ይሆነልኝን አስቤው ፡ ያን ፡ ዘመን ፡ በርሱ ፡ ያለፍኩትን ክበር ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ ንገሥ ፡ ልበለው ፡ እየደጋተምኩኝ ክበር ፡ ልበለው ፡ አከብረዋለሁኝ ንገሥ ፡ ልበለው ፡ አነግሰዋለሁኝ ቤቴ ፡ በክብሩ ፡ ተሞላና እኔም ፡ ወግ ፡ አየሁ ፡ እንደገና (፪x) ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ ሳልሰለች ፡ በደስታ ፡ ልዘምር ፡ ለጌታ ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ ምነው ፡ በሆንኩለት (፫x) ሕይወቴ ፡ ያማረው ፡ እርሱን ፡ ያገኘሁ ፡ እለት (፫x) አንደበቴን ፡ ልክፈት ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና (፫x) በቅቶኝ ፡ አልቀመጥ ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና (፫x) ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና (፪x) ይላል ፡ ገና ፡ ምሥጋና ይላል ፡ ገና ፡ ገናና ይላል ፡ ገና ፡ አምልኮ ይላል ፡ ገና ፡ ዝማሬ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.