Loading
አምኜው ፡ አልከዳኝም በእኔ ፡ ላይ ፡ አልፈረደም (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ ዳኛ ትክክል ፡ እውነተኛ (፪x) ሰው ፡ ፊትን ፡ አይቶ ፡ ሲፈርድ ፡ ጌታ ፡ ግን ፡ የልብን ፡ ነው ሁሉንም ፡ እንደስራው ፡ አይቶ ፡ ነው ፡ የሚከፍለው በፍርዱ ፡ አይጸጸት ፡ ለካ ፡ እንዲህ ፡ ነበር ፡ አይል አስተዋይ ፡ ጥበበኛ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ዳኛ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ ዳኛ ትክክል ፡ እውነተኛ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ፡ ተቀምጦ ፡ በችሎቱ አይፈራ ፡ አያዳላ ፡ አይዋሽም ፡ እንደሌላ አፉ ፡ በፍርድ ፡ አይስት ፡ ሚዛኑ ፡ ትክክል ፡ ነው በእኔ ፡ ላይ ፡ ሳይሆን ፡ ለእኔ ፡ ፈረደልኝ ፡ መድህኔ ዳኛዬ ፡ እሱ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ዳኛ (፬x) በግራና ፡ በቀኙ ፡ አማካሪ ፡ አይፈልግም ቃሉንም ፡ የሚያርመው ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ አይገኝም እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው ፡ ሥራውን ፡ ይመዝናል ውሳኔው ፡ መጨረሻው ፡ የእኔን ፡ ልብ ፡ አሳርፏል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ ዳኛ ትክክል ፡ እውነተኛ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.