Loading
በዕውቀትህ ፡ ቀላያት ፡ ተቀደዱ በማስተዋልህ ፡ ሰማያት ፡ ጸኑ ጥበብህ ፡ ምድርን ፡ መሠረተ ደመና ፡ ጠልን ፡ አንጠበጠበ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ በመጀመሪያ ፡ ሰማይንና ፡ ምድርን ፡ የፈጠርከው አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ብርሃንን ፡ ደግሞ ፡ ከጨለማ ፡ የለየኸው አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጠፈሩን ፡ ሰማይ ፡ የብሱንም ፡ ምድር ፡ ብለህ ፡ የጠራኸው አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የምድርን ፡ ባዶነት ፡ በቃልህ ፡ የሞላኸው ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብለህ ፡ ፈጥረህ ፡ በሙሉ ፡ የሆኑልህ እንደተናገርከው ፡ የሆነ ፡ እንዳሰብከው ፡ የቆመልህ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር በዕውቀትህ ፡ ቀላያት ፡ ተቀደዱ በማስተዋልህ ፡ ሰማያት ፡ ጸኑ ጥበብህ ፡ ምድርን ፡ መሠረተ ደመና ፡ ጠልን ፡ አንጠበጠበ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ተራሮችንም ፡ ኮረብቶችንም ፡ በሚዛን ፡ የመዘንከው አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የምድርን ፡ አፈር ፡ በመስፈሪያ ፡ የሰበሰብከው አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ከጥንት ፡ ጀምሮ ፡ በምድር ፡ ክበብ ፡ ላይ ፡ የተቀመጥከው አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ አማካሪ ፡ አትፈልግ ፡ ጥበብህ ፡ ቁጥር ፡ የሊለው ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብለህ ፡ ፈጥረህ ፡ በሙሉ ፡ የሆኑልህ እንደተናገርከው ፡ የሆነ ፡ እንዳሰብከው ፡ የቆመልህ ንግስናና ፡ ክብርን ፡ የለበስህ በማስተዋል ፡ እጅቅ ፡ ድንቅ ፡ የሆንህ ሃሳብህ ፡ ጥልቅ ፡ የማይመረመር ካልኩት ፡ በላይ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ በፊትህ ፡ ወድቆ ፡ የሚሰግድልህ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ እኩያ ፡ አምሳያ ፡ የለህ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ ሳይኖር ፡ ከሁሉ ፡ በፊት ፡ ብቻህን ፡ የነበርከው አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ሁሉመ ፡ ነገር ፡ ሲያልፍ ፡ ሲጠቀለል ፡ የምትኖረው ታዲያ ፡ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ያየ ፡ አትኩሮ ፡ ያስተዋለ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ከማለት ፡ በቀር ፡ የሚለው ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር ንግስናና ፡ ክብርን ፡ የለበስህ በማስተዋል ፡ እጅቅ ፡ ድንቅ ፡ የሆንህ ሃሳብህ ፡ ጥልቅ ፡ የማይመረመር ካልኩት ፡ በላይ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ እግዚአብሔር
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.