Loading
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ፡ የሞትክልኝ ፡ በእኔ ፡ ቦታ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ፡ የቆምክልኝ ፡ በእኔ ፡ ቦታ (ኧኸ) ፡ ጅማሬዬ ፡ ላይ ፡ (ኧኸ) ፡ ታሪክ ፡ ሲዘጉ (ኧኸ) ፡ ቁጣህ ፡ ነደደ ፡ (ኧኸ) ፡ አንተን ፡ እንደነኩ (ኧኸ) ፡ ወጪ ፡ ወራጁ ፡ (ኧኸ) ፡ የሚቀናበት (ኧኸ) ፡ ክብርህ ፡ ፈሰሰ ፡ (ኧኸ) ፡ ገባ ፡ ከእኔ ፡ ቤት አዝ፦ ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ አለኝታዬ ፡ (አለኝታዬ) ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ ከለላዬ ፡ (ከለላዬ) (፪x) (ኧኸ) ፡ ሲማማምሉና ፡ (ኧኸ) ፡ ሲማከሩብኝ (ኧኸ) ፡ ፍላጻህ ፡ ወርዶ ፡ (ኧኸ) ፡ አፈረሰልኝ (ኧኸ) ፡ በጠላት ፡ ቀዬ ፡ (ኧኸ) ፡ በጠላት ፡ መንደር (ኧኸ) ፡ ስለአለኝታዬ ፡ (ኧኸ) ፡ እስኪ ፡ ልዘምር አዝ፦ ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ አለኝታዬ ፡ (አለኝታዬ) ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ ከለላዬ ፡ (ከለላዬ) (፪x) ጠላቴ ፡ ብዙ ፡ ለፍቶ ፡ በእጁ ፡ ሊያስገባኝ ፡ ጓግቶ ፍቅርህ ፡ ያሰረው ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለኝ ፡ ሀሳቤ (፪x) አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ፡ የሞትክልኝ ፡ በእኔ ፡ ቦታ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ፡ የቆምክልኝ ፡ በእኔ ፡ ቦታ (ኧኸ) ፡ ማለዳ ፡ ቀትር ፡ (ኧኸ) ፡ ነግቶ ፡ እስኪመሽ (ኧኸ) ፡ በእኔ ፡ ዝማሬ ፡ (ኧኸ) ፡ ጠላት ፡ ሲረበሽ (ኧኸ) ፡ የማታው ፡ ለቅሶ ፡ (ኧኸ) ፡ ጠዋት ደስታ (ኧኸ) ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ (ኧኸ) ፡ ማረፍ ፡ በጌታ አዝ፦ ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ አለኝታዬ ፡ (አለኝታዬ) ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ ከለላዬ ፡ (ከለላዬ) (፪x) ጥቃቴን ፡ ከላይ ፡ አይተህ ፡ ክብርህን ፡ ለእኔ ፡ ትተህ ወርደህ ፡ ያወጣኸኝ ፡ ሞተህ ፡ ያተረፍከኝ (፪x) አዝ፦ ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ አለኝታዬ ፡ (አለኝታዬ) ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ ከለላዬ ፡ (ከለላዬ) (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.