Loading
የኑሮ ፡ መክበዱን ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ መወደዱ እህል ፡ ከጐተራ ፡ ሲጠፋ ፡ ፍሬም ፡ ባትሰጥ ፡ መሬት ፡ ታርሳ ቀና ፡ ብሎ ፡ ዓይን ፡ ሲያይ ፡ ደመና ፡ የለም ፡ በላይ ምድር ፡ ከሰማይ ፡ ይጠብቃል ፡ ሰማይ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አፍጡዋል ጊዜው ፡ ቢወስድ ፡ ይህ ፡ ዝምታ ፡ አምላኬ ፡ ምድሬን ፡ እየረሳ ግን ፡ ጨለማው ፡ መበርታቱ ፡ ሊነጋ ፡ ነው ፡ ሌሊቱ (፪x) አዝ፦ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ኦ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ኦ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ ፡ በምድሬ ፡ ሲነሳ የመከራው ፡ ዘመን ፡ ሲረሳ እምባ ፡ ካለቀሰው ፡ ሲታበስ የዘመናት/የአባቶቼ ፡ ጸሎት ፡ ሲመለስ (፪x) አያለሁ ፡ አያለሁ ፣ አያለሁ ፡ አያለሁ አዝ፦ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ኦ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ የጦርነት ፡ ድምጽ ፡ ፈርቶ ካደገበት ፡ ቀይ ፡ ሸሽቶ በሰው ፡ ሃገር ፡ አንገት ፡ የደፋ የተናቀን ፡ የተገፋ ምድረ ፡ በዳውን ፡ ሲያቋርጠው በረሃው ፡ ሁሉም ፡ ሱያስጥለው ግን ፡ ሃገሩን ፡ ይዞ ፡ በልቡ ተበትኗል ፡ ሰሜን ፡ ደቡቡ ተስፋ ፡ ቢጨልም ፡ በሁሉ ፡ ነገር አንደበት ፡ ግን ፡ ክፉ ፡ አይናገር ያለፈው ፡ ይብቃ ፡ እርግማኑ የምትሰማ ፡ አያለሁ (፪x) አዝ፦ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ኦ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ ሽባዎች ፡ አንካሶች ፡ ሲዘሉ ዲዳዎች ፡ ተናግረው ፡ ዕልል ፡ ሲሉ የታወረው ፡ ዓይን ፡ ሲበራ እግዚአብሔር/የማመልከው ፡ እራሱ ፡ ሲሰራ አያለሁ ፡ አያለሁ ፣ አያለሁ ፡ አያለሁ (፭x) ሃሌሉያ ፡ አያለሁ እኔ ፡ እኔ ፡ እኔ ፡ አያለሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.