Loading
ምን ፡ አጣሁኝ ፡ ብለህ ፡ ወጣህ ፡ ከአባትህ ፡ ቤት ሄድክ ፡ ርቀህ ፡ ሰላም ፡ ደስታ ፡ ወደ ፡ ሌለበት አባትህ ፡ አሁንም ፡ እቤት ፡ ካሉት ፡ ይልቅ ያሰባል ፡ ሰለአንተ ፡ ይናፍቃል ፡ ይጠብቃል ሚመለሰው ፡ ልጄ ፡ መቼ ፡ ነው ፡ እያለ የጠፋው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ አንተ ፡ አይደለህ ፡ ወይ መመለስህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ይናፍቃል ፡ ሊያይ መመለስህን ፡ ሁልጊዜ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይናፍቃል ፡ ሊያይ ና ፡ ተመለስ ፡ ሁሉን ፡ ትተህ ፡ እርሳውና የአባትህ ፡ እጅ ፡ ዛሬም ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ እንደተዘረጋ በትር ፡ ይዞ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ ሚጠብቅህ ታውቀዋለህ ፡ አንዳይለወጥ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሚወድህ "ወንድሜ ፡ ብዙዎች ፡ በቤቱ ፡ ቢኖሩም ስለጠፋኀው ፡ስለአንተ ፡ ዘወትር ፡ ያስባል ወደ ፡ ቤቱ ፡ የምትመለስበትን ፡ ሰዓት ፡ ይጠባበቃል የክብር ፡ ልብስ ፡ ሊያለብስህ የምህረት ፡ ደጆቹ ፡ ሁልጊዜ ፡ ለአንተ ፡ ክፍት ፡ ናቸው በአባትህ ፡ ቤት ፡ መኖር ፡ ለአንተ ፡ ይሻልሃል ወስነህ ፡ እንዲ ፡ በል" ኢሄው ፡ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ቤት ተመልሻለሁ ፡ እንድትምረኝ በክርስቶስ ፡ አስቀድሜ ፡ ተይቃለሁ እኔም ፡ ልጅህ ፡ ናፍቄያለሁ አባቴ ፡ አንተን ፡ ይሄው ፡ ልጅህ መጥቻለው ፡ ብትቀበለኝ ወድሃለሁ (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ወስኛለሁ አዲስ ፡ ጉዦ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ልጀምር ፡ ወስኛለሁ አዲስ ፡ ጉዦ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ልጀምር
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.