Loading
(ትዝ ፡ ይለኛል) አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x) ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ ከሞት ፡ የተረፍኩበት አስቤ ፡ አላደረኩት ፡ ቀጠሮም ፡ አልነበረኝ በድንገት ፡ በአጋጣሚ ፡ በስፍራው ፡ ተገኘሁኝ (ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ) ወደቤተ ፡ መቅደሱ ፡ ወደውስጠኛው ፡ ስገባ ተሰማኝ ፡ የእግዚአብሔር ፡ የአምላኬ ፡ ህልውና (ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ) አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x) ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ ከሞት ፡ የተረፍኩበት ሰሰማን ፡ ህልውናው ፡ በደስታ ፡ ውስጤ ፡ ሲሞላ ከዐይኖቼ ፡ ሲፈሱ ፡ የደስታ ፡ የሃሴት ፡ እምባ (ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ) እጆቼን ፡ ዌርሱ ፡ አንስቼ ፡ በቃ ፡ የአንተ ፡ ነኝ ፡ ስለው ለዘለዓለም ፡ ወስኜ ፡ ሕይወቴን ፡ ስሰጠው (ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ) አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x) ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ ከሞት ፡ የተረፍኩበት አንደበቴ ፡ ለክብርህ ፡ መከፈት ፡ ሲጀምር ሰዎችም ፡ ሲደነቁ ፡ በአደረክልኝ ፡ ነገረ (ግርም ፡ ይለኝ ፡ ጀመር) ይቅርታን ፡ ከአንተ ፡ ጠይቄ ፡ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ እንደገና ፡ በቤትህ ፡ አጽንተህ ፡ ስትተክለኝ (እጅግ ፡ ተደሰትኩኝ) አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x) ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ ከሞት ፡ የተረፍኩበት ማንነቴ ፡ ተቀይሮ ፡ አዲስ ፡ ፍጥረት ፡ ሆንኩኝ የኋላዬን ፡ ረስቼ ፡ የፊቴን ፡ እያየሁኝ (ጉዞዬን ፡ ጀመርኩኝ) ድል ፡ በድል ፡ እየጨመረ ፡ ነገሬ ፡ እያማረልኝ የሚያውቀኝ ፡ ሰው ፡ በሙሉ ፡ ሲገረም ፡ ሲደነቅብኝ (ጌታዬን ፡ አከበርኩኝ) አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x) ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ ከሞት ፡ የተረፍኩበት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.