Loading
አዝ:- ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና (፬x) ገና ፡ በልጅነት ፡ በልጅነት ፡ ስለለመድኩኝ ውለታህን ፡ እያሰብ ፡ እያሰብ ፡ አመሰገንኩኝ አሁን ፡ የምሥጋና ፡ ጥቅሙ ፡ ኃይሉ ፡ ሲገባኝ ከነገሬ ፡ በፊት ፡ አስቀድሜ ፡ አመሰገንኩኝ ምሥጋና ፡ ሲቀድም ፡ ሲወጣ ፡ ሲሆን ፡ መጀመሪያ አውቃለሁ ፡ በረከት ፡ . (1) . ፡ ፈጥኖ ፡ ለእኔ ፡ እንደሚመጣ አዝ:- ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና (፬x) ጠብቄ ፡ ጥያቄዬ ፡ ጥያቄዬ ፡ ሲመለስልኝ ምሥጋና ፡ ለአምላኬ ፡ ለአምላክ ፡ ሠጥ ፡ ቆየሁኝ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሲገባኝ ፡ ሲገባኝ ፡ ሲገለጥ ፡ ነገሩ በልጅ ፡ አንደበቴ ፡ አንደበት ፡ ምሥጋና ፡ ማኖሩ ጠላት ፡ ምቀኛዬ ፡ ምቀኛዬ ፡ ለማጥፋት ፡ ነው ፡ ለካ ስለዚህ ፡ ላመስግን ፡ ላመስግነው ፡ በምንም ፡ ሁኔታ አዝ:- ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና (፬x) ከፊቴ ፡ የቆመው ፡ ተራራ ፡ አይደለውም ፡ መናዱ ከሰማይም ፡ መና ፡ ወይም ፡ ሥጋ ፡ አይደለም ፡ መውረዱ ተራራው ፡ ሳይናድ ፡ ሳይናድ ፡ መናው ፡ ሳይወርድልኝ ይሁዳን ፡ ከፊቴ ፡ ከፊቴ ፡ አስቀድማለሁኝ ምሥጋና ፡ ሲቀድም ፡ ሲወጣ ፡ ሲሆን ፡ መጀመሪያ አውቃለሁ ፡ በረከት ፡ . (2) . ፡ ፈጥኖ ፡ ለእኔ ፡ እንደሚመጣ አዝ:- ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.