Loading
አዝ:- እቀድስሃለው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ በውጪ ፡ አይደለም ፡ ማደሪያህ ፡ ገብቼ ፡ ገብቼ (፪x) ድሮ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በፊት ፡ ገና ፡ ያኔ መስዋእቴን ፡ ለካህንህ ፡ ስሰጥ ፡ እኔ ፡ ውጭ ፡ ቆሜ ካህኑ ፡ የገባው ፡ እየቀደሰህ እኔም ፡ እመኝ ፡ ነበር ፡ ክብርህን ፡ ማየት ዛሬማ ፡ ሆነልኝ ፡ እኔም ፡ በልጅህ ደፍሬ ፡ እንድገባ ፡ ወደ ፡ መገኛህ አዝ:- እቀድስሃለው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ በውጪ ፡ አይደለም ፡ ማደሪያህ ፡ ገብቼ ፡ ገብቼ (፪x) ብዙዎች ፡ ያመልካሉ ፡ ስለማያውቁት ስፍራን ፡ ይመርጣሉ ፡ ለማቅረብ ፡ ለአንተ ፡ ስግደት እኔ ፡ ግን ፡ እያወኩ ፡ ገብቶኝ ፡ ማንነትህ በመንፈስ ፡ በእውነት ፡ ወደድኩኝ ፡ ላመልክህ ካህን ፡ አልፈልግም ፡ ረዳትስ ፡ ለእኔ እቀድስሃለሁ ፡ ብቻዬን ፡ መጥቼ አዝ:- እቀድስሃለው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ በውጪ ፡ አይደለም ፡ ማደሪያህ ፡ ገብቼ ፡ ገብቼ (፪x) መስዋእት ፡ አለ ፡ ከኔ ፡ ለአንተ ፡ ምሰጥህ ስለ ፡ አደረክልኝ ፡ አይደል ፡ ገብቶኝ ፡ እንጂ ፡ ማንነትህ በግሌ ፡ አወቅኩህ ፡ ወደድኩህ ፡ ከልቤ በማወቅ ፡ ተናገርሁ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ብዬ በማወቅ ፡ ተናገርሁ ፡ አዳኜ ፡ ነህ ፡ ብዬ በማወቅ ፡ ተናገርሁ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ብዬ አዝ:- እቀድስሃለው (፫x) ፡ ጌታዬ በውጪ ፡ አይደለም ፡ ማደሪያህ ፡ ገብቼ ፡ ገብቼ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.