Loading
አዝ:- አዋቂ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (፭x) አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው ጽንሷ ፡ መዘግየቱ ፡ ያሳዝናል ሃና ፡ ባትረዳ ፡ ባይገባት ጌታ ፡ በእርሷ ፡ ያየው ፡ ትልቅ ፡ ሰው አስቦ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ለእራሱ ፡ ሊለየው ረስታ ፡ ሃና ፡ የእግዚአብሔርን ፡ አዋቂነት ካሰበችው ፡ በላይ ፡ ሲሆን ፡ ድንገት የእርሱ ፡ ስራው ፡ ለጊዜ ፡ አስደናቂ አለች ፡ እርሷም ፡ ግርም ፡ ሲላት ፡ኧረ ፡ አዋቂ አዝ:- አዋቂ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (፭x) አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው ኤልያብ ፡ ነው ፡ በሰው ፡ ሚዛን ፡ የበለጠው በነቢዩ ፡ ዐይን ፡ እንኳን ፡ ቀድሞ ፡ የገባው ፊትን ፡ አልፎ ፡ ሚመረምር ፡ የልብን እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ መረጠው ፡ ዳዊትን የጓዳውን ፡ ሰው ፡ ሳያየው ፡ ስለሚያውቀው እረኛውን ፡ በስልጣን ፡ ላይ ፡ አስቀመጠው ጠብቆ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ስለሚያውቀው ሲመርጥ ፡ እርሱ ፡ አይሳሳትም ፡ አዋቂ ፡ ነው አዝ:- አዋቂ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (፭x) አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው የትኛውን ፡ ነገሬን ፡ ነው ፡ ምደብቀው እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ያያል ፡ አዋቂ ፡ ነው በሰዎች ፡ መመረጥ ፡ ቀርቶብኝ ይሁንልኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያየልኝ ጅማሬውን ፡ ፍጽሜውን ፡ ስለሚያውቀው ይሻለእኛል ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ እርሱ ፡ ያለው መልካም ፡ ስለሆነ ፡ የሚያስበው የመረጠው ፡ እርሱ ፡ ለእኔ ፡ ምርጫዬ ፡ ነው አዝ:- አዋቂ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (፭x) አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.