Loading
የሰው ፡ አስታማሚ ፡ ውሱን ፡ ነው ፡ ስልቹ ይርዳሉ ፡ እጆቹ ፡ ይከብዳሉ ፡ ዓይኖቹ የሰው ፡ አስታማሚ ፡ ጥቂት ፡ ነው ፡ ትዕግስቱ እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ታማኝ ፡ ቅርብ ፡ ለጠሩቱ እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ታማኝ በራችሁ ፡ ተዘግቶ ፡ ተረሳን ፡ ያላችሁ ውኃ ቀና ፡ አድርጐ ፡ ጠፍቶ ፡ የሚያጠጣችሁ በሩቁም ፡ በቅርቡ ፡ በያላችሁበት ቁስላችሁ ፡ ይጠገን ፡ በጌታ ፡ ምህረት ቁስላችሁ ፡ ይጠገን ማነው ፡ የሚገደው ፡ ለእነኛ ፡ አቅም ፡ ላጡት ፀሐይ ፡ ለማይሞቁ ፡ ደጅ ፡ ለማይውጡ ከዓይናችን ፡ ከጠፉ ፡ ፈጥነው ፡ ይረሳሉ ኩርሲያቸው ፡ ተወስዶ ፡ እያሉ ፡ እንደሌሉ አዝ፦ ከአጥር ፡ ውዲህ ፡ ተከማችተን ጭፍራ ፡ ዝላዩን ፡ ትተን እስቲ ፡ እንውጣ ፡ ከአዳራሹ ፍቅር ፡ ድጋፍ ፡ ወደሚሹ ፌጦው ፡ ድንገተኛው ፡ ሁሉ ፡ ተሞክሮ ሃኪሙም ፡ ሳይታክት ፡ በጥበብ ፡ በአይምሮ በሩቅ ፡ በጐረቤት ፡ ተመክሮ ፡ ተዘክሮ እልፍ ፡ አልተገኘም ፡ ተጥሮ ፡ ተግሮ በህክምና ፡ ሂደት ፡ መድኃኒት ፡ ቅመማ በሳይንስ ፡ ጥናት ፡ በሊቆች ፡ ግምገማ የዕድሜያችሁ ፡ መጽሃፍ ፡ ተከድኗል ፡ ያሉአችሁ ወደ ፡ ፈዋሽ፡ አምላክ ፡ ይመልከት ፡ ዓይናችሁ ወደ ፡ ፈዋሽ፡ አምላክ ማነው ፡ የሚገደው ፡ ለእነኛ ፡ አቅም ፡ ላጡት ፀሐይ ፡ ለማይሞቁ ፡ ደጅ ፡ ለማይውጡ ከዓይናችን ፡ ከጠፉ ፡ ፈጥነው ፡ ይረሳሉ ኩርሲያቸው ፡ ተወስዶ ፡ እያሉ ፡ እንደሌሉ አዝ፦ ከአጥር ፡ ውዲህ ፡ ተከማችተን ጭፍራ ፡ ዝላዩን ፡ ትተን እስቲ ፡ እንውጣ ፡ ከአዳራሹ ፍቅር ፡ ድጋፍ ፡ ወደሚሹ ህመማችሁ ፡ ጸንቶ ፡ ቀና ፡ የማትሉት ፋታ ፡ የማይሰጣችሁ ፡ ውጋት ፡ ቀርጥማቱ ውሉ ፡ የጠፋችሁ ፡ የቀን ፡ የሌሊቱ ጌታ ፡ ይዳብሳችሁ ፡ ባላችሁበቱ በበሽታ ፡ አቅምህ ፡ የለ ሥጋ ፡ አጥንትህ ፡ የሰለለ በፍራቻ ፡ ባሕር ፡ ስምጠት ሰውም ፡ ከቦህ ፡ ብቸኝነት ከሃኪሙ ፡ ተስፋ ፡ አጥተሃል ጤና ፡ አዳሙም ፡ ሰልችቶሃል እዛው ፡ ባልጋው ፡ ባለህበት ፈዋሹ ፡ አምላክ ፡ ይንካህ ፡ ድንገት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.