Loading
የደን ፡ ልማቱ ፡ የገደል ፡ ስርገቱ የወንዝ ፡ እርዝመቱ ፡ የቀላይ ፡ ውበቱ የቆንጆ ፡ ገጽታው ፡ የቦታ ፡ ከፍታው የባሕር ፡ ጥልቀቱ ፡ የሜዳ ፡ ስፋቱ እኛ ፡ ምናመልከው ፡ መሠረቱ አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምንሰግድለት የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት የሽቶ ፡ መዓዛው ፡ የሙዚቃ ፡ ቃናው የለምለም ፡ እርካታው ፡ የመዝናኛ ፡ ቦታው የመፋቅር ፡ ወዙ ፡ የትዳር ፡ ማገዙ የፍጥረት ፡ ድምቀቱ ፡ የሰማይ ፡ ርቀቱ እኛ ፡ ምናመልከው ፡ መሠረቱ አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምንሰግድለት የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት የአበቦች ፡ ፍካታ ፡ የወፎች ፡ ጫጫታ የቀለም ፡ መዋሃድ ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ መዋደድ የእምነት ፡ እርካታ ፡ ሰላምና ፡ ደስታ የፅዮን ፡ ውበቱ ፡ የእውነት ፡ ጥራቱ እኛ ፡ ምናመልከው ፡ መሠረቱ አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምንሰግድለት የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት ጐህ ፡ ሲቀድ ፡ ማለዳ ፡ ጨለማ ፡ ሲከዳ የፀሐዩ ፡ ሙቀት ፡ የከዋክብት ፡ ብዛት የደመናት ፡ ክምር ፡ ንጹህ ፡ ተስማሚ ፡ አየር ሁሉን ፡ በስርዓቱ ፡ መሪ ፡ ለፍጥረቱ እኛ ፡ ምናመልከው ፡ መሠረቱ አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምንሰግድለት የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.