Loading
አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል ጌታ ፡ ይመራሃል የማዕበሉ ፡ ጌታ ፡ ቀድሞሃል ተከተለኝ ፡ አይዞህ ፡ ይልሃል ቀና ፡ ነው ፡ መንገዱ ፡ ተጽናና የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ አለና አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል ጌታ ፡ ይመራሃል ባሕሩ ፡ አፍ ፡ ለአፍ ፡ ሞልቶ ወጀብ ፡ ሲያናውጠው ፡ በርትቶ ሰንጥቀህ ፡ ማለፍን ፡ ብትፈራ ቶሎ ፡ ብለህ ፡ ጌታህን ፡ ጥራ አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል ጌታ ፡ ይመራሃል ሁሉንም ፡ በቃሉ ፡ ያዘዋል ፍጥረትም ፡ ለእርሱ ፡ ይታዘዛል ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከፊትህ ጠላት ፡ ሲረፈረፍ ፡ ታያለህ አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል ጌታ ፡ ይመራሃል በባሕሩ ፡ ጉዞ ፡ ብትዝልም አይዞህ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ አትቀርም ጌታህ ፡ አጠገብህ ፡ አለና እርዳኝ ፡ በለው ፡ ጠጋ ፡ በልና አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ ታምነህ ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል ጌታ ፡ ይመራሃል (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.