Loading
1. የዕውቀት ፡ ራስ ፡ የጥበብ ፡ ጌታ ምንም ፡ ቢፈተን ፡ የማይረታ በሰው ፡ አእምሮ ፡ አይገመትም ወርዱም ፡ ስፋቱም ፡ አይዘልቅም አዝ፦ አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ አመልካለሁ ፡ በማንም ፡ የማይረታ አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁትን አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ ዕራስን 2. ፍቅሩን ፡ አይቼ ፡ ቀምሸዋለሁ ፍጹም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ በመከራዬ ፡ እርሱ ፡ እየገባ ይጋፈጠዋል ፡ እንዳልረታ አዝ፦ አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ አመልካለሁ ፡ በማንም ፡ የማይረታ አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁትን አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ ዕራስን 3. ጥፋቴን ፡ ሁሉ ፡ በፍቅር ፡ እያየ ያሳልፈኛል ፡ ልጄ ፡ እያለ ከሁሉም ፡ በፊት ፡ ፍቅሩ ፡ ሰብሮኛል በመስቀሉ ፡ ላይ ፡ ነፍሱን ፡ ሰጥቶኛል አዝ፦ አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ አመልካለሁ ፡ በማንም ፡ የማይረታ አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁትን አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ ዕራስን 4. ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም እንደርሱ ፡ የሚሆን ፡ ከቶ ፡ አላገኝም የውስጥ ፡ ችግሬን ፡ ሳልነግረው ፡ ያውቃል ለእኔ ፡ ሲከብደኝ ፡ ይሸከመዋል አዝ፦ አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ አመልካለሁ ፡ በማንም ፡ የማይረታ አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁትን አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ ዕራስን
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.