Loading
ስለዚህ ፡ እላችኋለሁ ፡ ስለ ፡ ነፍሳችሁ ፡ በምትበሉትና ፡ በምትጠጡት ፡ ወይም ፡ ስለ ፡ ሰውነታችሁ ፡ በምትለብሱት ፡ አትጨነቁ ። ነፍስ ፡ ከመብል ፡ ሰውነትም ፡ ከልብስ ፡ አይበልጥምን? ወደ ፡ ሰማይ ፡ ወፎች ፡ ተመልከቱ ። አይዘሩም ፡ አያጭዱም ፡ በጐተራም ፡ አይከቱም ። የሰማዩ ፡ አባታችሁ ፡ ይመግባቸዋል ። እናንተም ፡ ከእነርሱም ፡ እጅግ ፡ አትበልጡምን? ከእናንተ ፡ ተጨንቆ ፡ ከቁመቱ ፡ ላይ ፡ አንድ ፡ ክንድ ፡ መጨመር ፡ የሚችል ፡ ማነው? ስለልብስስ ፡ ስለምን ፡ ትጨነቃላቹህ? የሜዳ ፡ አበቦች ፡ እንዴት ፡ እንዲያድጉ ፡ ልብ ፡ አድርጋችሁ ፡ ተመልከቱ ። አይደክሙም ፤ አይፈትሉምም ። ነገር ፡ ግን ፡ እላችኋለሁ ፡ ሰለሞንስ ፡ እንኳን ፡ በክብሩ ፡ ሁሉ ፡ ከነዚህ ፡ እንደ ፡ አንዱ ፡ አልለበሰም ። እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ዛሬ ፡ ያለውን ፡ ነገም ፡ ወደ ፡ እቶን ፡ የሚጣለውን ፡ የሜዳን ፡ ሳር ፡ እንዲህ ፡ የሚያለብሰው ፡ ከሆነ ፣ እናንተ ፡ እምነት ፡ የጐደላችሁ ፡ እናንተንማ ፡ ይልቁን ፡ "እንዴት ፡ እንግዲህ ፡ ምን ፡ እንበላለን? ምንስ ፡ እንጠጣለን? ምንስ ፡ እንለብሳለን?" ብላችሁ ፡ አትጨነቁ ። ይህንስ ፡ ሁሉ ፡ አሕዛብ ፡ ይፈልጋሉ ። ይህ ፡ ሁሉ ፡ እንዲያስፈልጋችሁ ፡ የሰማዩ ፡ አባታችሁ ፡ ያውቃልና ። ነገር ፡ ግን ፡ አስቀድማችሁ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ መንግስት ፣ ጽድቁንም ፡ ፈልጉ ። ይህም ፡ ሁሉ ፡ ይጨመርላችኋል ። ነገ ፡ ለራሱ ፡ ይጨነቃልና ፡ ለነገ ፡ አትጨነቁ ። ለቀኑ ፡ ክፋቱ ፡ ይበቃዋል ። ነገ ፡ ለራሱ ፡ ይጨነቃልና ፡ ለነገ ፡ አትጨነቁ ። [1] አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ ነገ ፡ ለሚሆነው ፡ ብጨነቅ ፡ ባዝን ትርፉ ፡ ማጉረምረም ፡ ነው ፡ ጌታንም ፡ ማሳዘን ጨንቀቴን ፡ ሁሉ ፡ ለጌታ ፡ ማስረከብ ፡ ነው ስለእኔ ያስባል ፡ እርሱ ፡ አባቴ ፡ ነው የእኔ ፡ ነገ ፡ ሙሉ ፡ ፀሐይ ፡ ነው የሚያዝበትም ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ የነገ ፡ ውለቴ ፡ በጌታ ፡ እጅ ፡ ነው ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ በእርሱ ፡ ቁጥጥር ፡ ነው የሰማዩ ፡ አባቴ ፡ በነገው ፡ አልፎበታል ደመናው ፡ ይጠፋል ፡ ሃዘን ፡ ደስታ ፡ ይሆናል የእኔ ፡ ነገ ፡ ተስፋ ፡ ያለው ፡ ነው ተቆጣጣሪው ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ ፈተናም ፡ ችግር ፡ መከራም ፡ ቢሆን ያለአባቴ ፡ ፈቃድ ፡ አንዳችም ፡ ላይሆን ፈቃዱም ፡ ከሆነ ፡ ክፉ ፡ ለበጐ ፡ ነው የኔም ፡ ነገ ፡ ሁልጊዜም ፡ ብርሃን ፡ ነው የእኔ ፡ ነገ ፡ ብሩህ ፡ ፀሐይ ፡ ነው የሚያዝበትም ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ ሞት ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ ለእኔ ፡ ጥቅም ፡ ነው ከጌታ ፡ ጋር ፡ መሆን ፡ እጅግ ፡ የሚሻል ፡ ነው ጨለማ ፡ ይጠብቀኝ ፡ ተስፋዬ ፡ ብሩህ ፡ ነው የፍጻሜው ፡ እድሌ ፡ የኔስ ፡ ትንሳኤ ፡ ነው የእኔ ፡ ነገ ፡ ፍፁም ፡ ብርሃን ፡ ነው ይሁን ፡ ያለውም ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.