Loading
ጉባኤውን ፡ ሁሉ ፡ ባርከው ፡ ጌታ ቃልህን ፡ ላክ ፡ ፈውስ ፡ ይሁንልን በታላቅ ፡ መጐብኘትህ ፡ አስበን የኋለኛውን ፡ ዝናብህን ፡ ላክልን እሳት ፡ እሳት ፡ ያንን ፡ የመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እሳት (፪x) ጉባኤውን ፡ ተመልከተው ፡ ጌታ የደከመውን ፡ ሁሉ ፡ አንሳ የላሉትንም ፡ ጉልበቶቼን ፡ ሁሉ ለአምላካቸው ፡ ሁሉ ፡ አበርታ ልጆቼ ፡ አይዟችሁ ፡ በለን ፡ ጌታ (፪x) የታመሙትንም ፡ ሁሉ ፡ ፈውስ በታላቅ ፡ ምህረትህ ፡ አስበን የታሰሩትንም ፡ ሁሉ ፡ ፍታ ጐብኘን ፡ የሠራዊት ፡ ጌታ ተነስ ፡ ተነስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ ፡ ሆይ ፡ ተነስ (፪x) ታላቁ ፡ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ጌታ ምህረትህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጠዋት ፡ ማታ ማዳንህ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ ክብርህ ፡ ይስፋ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ለዘለዓለም ፡ ክበር ፡ ሃሌሉያ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.