Loading
የባርነት ፡ ኑሮ ፡ ሰልችቷቸው ፡ ተመረዉ ቅድስቲቷን ፡ ከተማ ፡ ተመኝተው ፡ ፈልገዋት ተጨንቀህ ፡ ተጠበህ ፡ ያወጣሃቸው ፡ ምርጥህ ፡ ሕዝቦች የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ጌታዬ ፡ ደምህ ፡ ፍሬዎች አዝ፦ ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ የወጡት የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ከነአንን ፡ ሳያይዋት ጌታ ፡ መልሳቸው ፡ ወደ ፡ መንጐችህ ፡ በረት በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ሳይደርስባቸው ፡ የፍርድ ፡ እለት ሲያለቅሱ ፡ በምኞት ፡ እጅግ ፡ ናፍቀው ፡ ያቺን ፡ ሃገር ደግሞም ፡ እየጠጡ ፡ የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ በፍቅር ጸጋር ፡ በዝቶላቸው ፡ የነበሩት ፡ በአገልግሎት ምን ፡ ጠቃሚ ፡ አገኙና ፡ ጥለውህ ፡ ሄዱ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ አዝ፦ ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ የወጡት የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ከነአንን ፡ ሳያይዋት ጌታ ፡ መልሳቸው ፡ ወደ ፡ መንጐችህ ፡ በረት በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ሳይደርስባቸው ፡ የፍርድ ፡ እለት በምህረትህ ፡ አቅፈህ ፡ አሳድገህ ፡ በአንተ ጉያ እንዴት ፡ ይችሉታል ፡ የበረሃውን ፡ መሰማሪያ የሕይወቱን ፡ ውኃ ፡ እየጠጡ ፡ ያደጉትን እንዴት ፡ ይችሉታል ፡ የበረሃውን ፡ ጥማትን አዝ፦ ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ የወጡት የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ከነአንን ፡ ሳያይዋት ጌታ ፡ መልሳቸው ፡ ወደ ፡ መንጐችህ ፡ በረት በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ሳይደርስባቸው ፡ የፍርድ ፡ እለት የደምህን ፡ ፍሬ ፡ ዘርተህ ፡ ነበር ፡ በጭንቅ ፡ ጌታ አድገዋል ፡ ሲባሉ ፡ ጠወለጉና ፡ ጠፉ ፡ ጌታ ኧረ ፡ መልሳቸው ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለደምህ ወደ ፡ ለምለም ፡ ይምጡ ፡ ከበረሃው ፡ ግልገሎችህ አዝ፦ ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ የወጡት የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ከነአንን ፡ ሳያይዋት ጌታ ፡ መልሳቸው ፡ ወደ ፡ መንጐችህ ፡ በረት በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ሳይደርስባቸው ፡ የፍርድ ፡ እለት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.