Loading
አዝ፦ የጽዮን ፡ ግርማዋ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በላይ ፡ ያለው የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ደግሞም ፡ የሚባለው እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ጌታችን ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው ምድር ፡ መረገጫው ፡ ሰማይም ፡ ዙፋኑ የጽዮን ፡ ሙሽራ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ብርሃኑ ወጀብ ፡ ነጐድጓድም ፡ ለርሱ ፡ ይታዘዛል ስሙ ፡ ግሩም ፡ መንፈስ ፡ ነው ፡ ሰላምን ፡ ይሰጣል አዝ፦ የጽዮን ፡ ግርማዋ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በላይ ፡ ያለው የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ደግሞም ፡ የሚባለው እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ጌታችን ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ደግሞም ፡ እሩህሩህ ፡ ነው ከአንበሳ ፡ መንጋጋ ፡ ከእሳት ፡ ያወጣ ፡ ነው ልጆቹን ፡ ይወዳል ፡ እህል ፡ ይሰጣቸዋል ቃሉም ፡ ለዘለዓለም ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ይኖራል አዝ፦ የጽዮን ፡ ግርማዋ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በላይ ፡ ያለው የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ደግሞም ፡ የሚባለው እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ጌታችን ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነው ፡ ዘመን ፡ አይሽረውም ሰማይ ፡ ምድር ፡ ሲያልፉ ፡ እርሱ ፡ አይለወጥም ስሙም ፡ ለዘለዓለም ፡ ታምርን ፡ ይሰራል ደሙ ፡ ፍጹም ፡ ኃይል ፡ ነው ፡ ሕይወትን ፡ ይሰጣል አዝ፦ የጽዮን ፡ ግርማዋ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በላይ ፡ ያለው የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ደግሞም ፡ የሚባለው እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ጌታችን ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.