Loading
ለሰው ፡ ሁሉ ፡ የሚያበራው እውነተኛው ፡ የዓለም ፡ ብርሃን በዓለም ፡ ውስጥ ፡ የነበረው ዓለሙ ፡ ግን ፡ ያላወቀው አዝ፦ እነሆ ፡ የዓለምን ፡ ኃጢአት ፡ የሚያስወግድ ዮሐንስ ፡ የመሰከረለት ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ (፪x) ለተቀበሉት ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ በስሙም ፡ ለሚያምኑም የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ይሆኑ ፡ ዘንድ ስልጣንንም ፡ ሰጣቸው አዝ፦ እነሆ ፡ የዓለምን ፡ ኃጢአት ፡ የሚያስወግድ ዮሐንስ ፡ የመሰከረለት ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ (፪x) እውነትን ፡ ተሞልቶ ፡ በእኛ ፡ ውስጥ ፡ ያደረ ኢየሱስ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ቀኝ ፡ የከበረ እግዚአብሔርን ፡ የለም ፡ ያየው በአባቱ ፡ እቅፍ ፡ ያለው ፡ ግን ፡ ተረከው አዝ፦ እነሆ ፡ የዓለምን ፡ ኃጢአት ፡ የሚያስወግድ ዮሐንስ ፡ የመሰከረለት ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.