Loading
ኢየሱስ ፡ ከስም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ስሙ ፡ ኃያል ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ፊቱ ፡ ተንበርክኮ ፡ ለእርሱ ፡ ይሰግዳል አይቆምም ፡ ማንም ፡ ፊቱ ፡ እሳት ፡ ነው ፡ ለጠላቱ አምላኬ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ኢየሱስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ፤ የሱሴ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ጌታዬ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ፤ ኢየሱሴ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ አሃ ፡ ለተቀበሉት ፡ አሃ ፡ በእርሱ ፡ ለሚያምኑት የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ይሆኑ ፡ ዘንድ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ጌታዬ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ፤ ኢየሱስ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ጌታዬ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ፤ አሃ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ግንበኞች ፡ የናቁት ፡ ድንጋይ እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ ፡ ሆነ እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ ፡ ሆነ እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ ከስም ፡ በላይ ፡ ስምን ፡ ሰጥቶ እግዚአብሔር ፡ ያለልክ ፡ ያከበረው ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ጌታዪ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ንጉሤ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ አባቴ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ አዳኜ ፡ ነው ያድናል ፡ የሚጠራውን ፡ ያድናል ፡ የታመነውን ያድናል ፡ በልቡ ፡ ዙፋን ፡ ያድናል ፡ ያነገሠውን ኢየሱስ ፡ ከሞት ፡ የማምለጫ ፡ ጽኑ ፡ አለት ሰው ፡ ሁሉ ፡ ስሙን ፡ እየጠራ ፡ ሚድንበት ሕይወት ፡ ነው ፡ የዘለዓለም ፡ የሚያድን ፡ ከጠፊው ፡ ዓለም ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም ሕይወት ፡ ነው ፡ የዘለዓለም ፡ ከእሱ ፡ በቀር ፡ አዳኝ ፡ የለም ንጉሥ ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ፡ አዳኝ ፡ የለም አሃ ፡ ለተቀበሉት ፡ አሃ ፡ በእርሱ ፡ ለሚያምኑት የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ይሆኑ ፡ ዘንድ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ጌታዬ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ፡ ኢየሱስ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ጌታዬ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ፡ አሃ ፡ ስልጣን ፡ ሰጣቸው ይሄ ፡ ስም ፡ ነው ፡ መዳኛዬ በክፉ ፡ ቀን ፡ ማምለጫዬ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መዳኛዬ በክፉ ፡ ቀን ፡ ማምለጫዬ (፫x) ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ ላላይ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ ሾሜዋለሁ ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ እኔስ ፡ በላዬ ፡ ላይ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ (ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ) (፮x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.