Loading
ዛሬም ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ሆ ዛሬም ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና አምላኬ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ገናና ገናና ፡ አዎ ፡ ዛሬም ፡ ገናና (፫x) ኢየሱስ ፡ ገናና (፪x) አዝ፦ ከለላዬ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ስንቱን ፡ ጌታ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ አዎ ፡ ስንቱን ፡ ጌታ (፪x) ንጉሥ ፡ ያከብረው ፡ ዝነድ ፡ እርሱ ፡ ለወደደው (፪x) ይህ ፡ ይደረጋል ፡ ከልካይ ፡ ኧረ ፡ ማነው (፪x) በንጉሥ ፡ ፈረስ ፡ ላይ ፡ ያስቀምጠውና (፪x) ይሸላልመዋል ፡ ዘይት ፡ ቀባና (፪x) አዝ፦ ከለላዬ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ስንቱን ፡ ጌታ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ አዎ ፡ ስንቱን ፡ ጌታ (፪x) በጉልበትህ ፡ ጽናት ፡ ሁሉን ፡ የምትገዛ (፪x) አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ ፡ የዓለም ፡ ሁሉ ፡ ቤዛ (፪x) ዛሬም ፡ ተማምኜ ፡ በጥላህ ፡ አድራለሁ (፪x) ንተ ፡ እያለህልኝ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ (፪x) አዝ፦ ከለላዬ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ስንቱን ፡ ጌታ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ አዎ ፡ ስንቱን ፡ ጌታ (፪x) ወሮታው ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ለአምላኬ ፡ ውለታ (፪x) እስኪ ፡ ከፍ ፡ አድርጉልኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ በዕልልታ (፪x) ወሮታው ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ለአምላኬ ፡ ውለታ (፪x) እስኪ ፡ ከፍ ፡ አድርጉልኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ በዕልልታ (፪x) ጭብጨባም ፡ ለጌታ (፪x) አዎ ፡ ዕልልታም ፡ ለጌታ (፪x) ጭብጨባም ፡ ለጌታ (፪x) ፡ አዎ ፡ ዕልልታም ፡ ለጌታ (፪x) ጭብጨባም ፡ ለጌታ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.