Loading
ዛሬ ልጅ ተብዬ ክብርን አግኝቻለሁ የቀድሞ ኑሮዬን ረስቼዋለሁ ታሪኬን ለውጠህ ሰው አድርጐ አቆመኝ የመረጥኩህ ልጄ እስራኤል ሆይ አለኝ የመረጥኩህ ልጄ የምወድህ ሆይ አለኝ አዝ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው ይድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (፪x) በክርስትናዬ እድሜን ቆጥሬያለሁ በልማዳዊ ሕይወት ተመላልሻለሁ ዛሬ ግን ኢየሱስ ነፍሴ አወቀችህ አምላኬ ጌታዬ ውዴ ነህ አለችህ አምላኬ ጌታዬ አባቴ አለችህ አዝ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (፪x) የስጋዬን ሳስብ እንዲያው ስቅበዘበዝ ጠላት ቤቴ ገብቶ ምርኮን ሲበዘብዝ እርሱ ግን ጌታዬ አሰበኝ ለአንድ አፍታ ኃይሌም ተመለሰ ጠላቴም ተረታ ኃይሌም ተመለሰ ይክበር የእኔ ጌታ አዝ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.