Loading
ዝናህን ፡ ላውራ ፡ ኦሆሆሆ ፡ ታላቅነትህን ስላንተ ፡ ዝና ፡ አውርቼ ፡ አልጠግብም ብናገር ፡ ብናገር (፪x) ኦ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ኦ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ትልቅ ፡ ነህ (፬x) ትልቅ ፡ ነህ (፬x) ቀና ፡ ብዬ ፡ ሠማዩን ፡ ሳይ ጨረቃዋን ፡ ከዋክብቱን ፡ ሳይ አሻቅቤ ፡ ተራራውን ፡ ሳይ ባሕሩን ፡ ውቅያኖሱን ፡ ሳይ አፈጠጠሩ ፡ ይገርመኛል አቤት ፡ ውበቱ ፡ ይደንቀኛል ጌታዬ ፡ የአንተን ፡ ትልቅነት ፡ ያሳየኛል አመልክሃለሁ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ አመልክሃለሁ ፡ ፊትህ ፡ ተደፍቼ አመልክሃለሁ ፡ ክብሬን ፡ ሁሉ ፡ ትቼ አመልክሃለሁ ፡ ወድጄ ፡ ፈቅጄ ኦ ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ እኔም ፡ አላውቅህም (፪x) ኦ ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ እኛም ፡ አናውቅህም (፪x) የፍጥረታት ፡ ሁሉ ፡ ፈጣሪ የማትመረመር ፡ መርማሪ ጥበብህን ፡ ዕውቀትህን ፡ ማን ፡ ያውቀዋል ፍርድህም ፡ ከማስተዋል ፡ ሁሉ ፡ ይልቃል ኦ ፡ ለመንገድህ ፡ ፍለጋ ፡ የለው አደራረግህ ፡ እጅግ ፡ ጥልቅ ፡ ነው አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ትልቅ ፡ ነህ (፬x) ትልቅ ፡ ነህ (፬x) ውሆችን ፡ በእፍኝህ ፡ የሰፈርህ ተራሮችን ፡ በሚዛን ፡ የመዘንህ ሠማዩን ፡ በስንዝር ፡ የለካህ የምድርን ፡ አፈር ፡ ሰብስበህ ፡ የያዝህ ሁሉን ፡ ስትሰራ ፡ ማን ፡ አማክሮሃል የፍርድን ፡ መንገድ ፡ ማን ፡ አስተምሮሃል አቤት ፡ ጥበብህ ፡ ከሁሉ ፡ ይልቃል ኦ ፡ አመልካህለሁ ፡ አሃ ፡ አመልክሃለሁ አሁ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ ኦ ፡ አመልካህለሁ ፡ አባ ፡ አመልክሃለሁ አሁ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.