Loading
የከበረ ፡ ከሁሉ ፡ የተሻለ የከበረ ፡ ከሁሉ ፡ የተሻለ ሰውነቴ ፡ ለአንተ ፡ አቀርባለሁ (፪x) እኔነቴን ፡ ለአንተ ፡ አቀርባለሁ (፪x) መሰዊያን ፡ ሰራሁ ፡ ልሰዋልህ ፡ በፊትህ ፡ ላቀርበው ያለኝን ፡ በሙሉ ፡ ታውቀዋለህ ፡ የቱን ፡ ነው ፡ ምትሻው እያልኩኝ ፡ ስደረድር ፡ ምድርና ፡ ሞላዋ ፡ ለካስ ፡ የአንተ ፡ ነው የሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ደስ ፡ እንዳያሰኝህ ፡ ይህንን ፡ ተረዳሁ ታዲያ ፡ እኔም ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ ምን ፡ ሰጥቼ/ሰውቼ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ እያልኩኝ ፡ ስጠይቅ ፡ ቃልህን ስጠው/ሰዋው ፡ አለኝ ፡ እራስህን (፪x) ስለዚህ ፡ እራሴን ፡ ሕያውና ፡ ቅዱስ ፡ አድርጌ ፊትህን ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘሁ ፡ ፈቀድኩኝ ፡ ልሰዋ ፡ ይኸው ልዩ ፡ ጣዕም ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ ሆኜ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ ፡ ጎይታ ከሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ጋራ ፡ ወደፊትህ ፡ እመጣለሁ የአምልኮዬ ፡ መዓዛ ፡ ሽታ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው በምህረት ፡ የተሞላህ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና አሁንም ፡ አበዛለሁ ፡ ከነፍሴ ፡ ምሥጋና ኦ ፡ በምሥጋና ፡ በዝማሬ ፡ እመጣለሁ ኦሆሆ ፡ ወደ ፡ ማደሪያህ ፡ እገባለሁ (፮x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.