Loading
ገመድ ፡ በአንገቴ ፡ ሳይገባ እጅም ፡ ሰንሰለት ፡ ሳያስረው እግሬ ፡ እየዘለለ ፡ አየተወራጨሁ ታዲያ ፡ የምን ፡ እስራት ፡ ነው ታዲያ ፡ የምን ፡ እስራት ፡ ነው አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስውር ፡ እስሬን ፡ አሳየኝ እንዳልራመድ ፡ ያደረገኝ ፡ አሳየኝ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስውር ፡ እስሬን ፡ አሳየኝ እንዳልራመድ ፡ ያደረገኝ ፡ አሳየኝ ዓይኔ ፡ እያየ ፡ በሚያልፈው ፡ ላይ እንዳልዘረጋ ፡ እጄን ፡ መዘዙን ፡ ሳላይ (እባክህ ፡ እርዳኝ) እንድጋልብበት ፡ ሲያምረኝ ፡ ፈረሱ ልጓም ፡ ከሌለው ፡ ይቅርብኝ ፡ እርሱ (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስውር ፡ እስሬን ፡ አሳየኝ እንዳልራመድ ፡ ያደረገኝ ፡ አሳየኝ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስውር ፡ እስሬን ፡ አሳየኝ እንዳልራመድ ፡ ያደረገኝ ፡ አሳየኝ ከንጉሥ ፡ ገበታ ፡ ከቃሉም ፡ ማዕድ ሁሌም ፡ ማልጠፋ ፡ ሆኜ ፡ የንጉሥ ፡ ልጅ ምነው ፡ መክሳቴ ፡ ምነው ፡ መመንመኔ የዓለም ፡ ቤዛ ፡ ሆነኀኝ ፡ መድህኔ (፪x) ገመድ ፡ ከአንገቴ ፡ ሸክም ፡ ከጫንቃዬ ይሰበር ፡ የእግር ፡ ብረቱ ይቆረጥ ፡ ከእጄ ፡ ሰንሰለቱ ፍታልኝ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ ፍታልኝ ፡ እስሬን ፡ ፍታልኝ ፍታልኝ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ ፍታልኝ ፡ ውዴ ፡ ፍታልኝ (፪x) ፍታልኝ ፡ ፍታልኝ ኢየሱስ ፡ እስሬን ፡ ፍታልኝ አባቴ ፡ አባቴ ፡ ፍታልኝ ፍታልኝ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.