Loading
በዚያ ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ በጨለማ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ጩኸቴን ፡ ሰማ (፪x) ደጃፌን ፡ ዘግቼ ፡ ያኔ ፡ የነገርኩህ (፪x) ያን ፡ ቀን ፡ ታስቦልኝ ፡ በእርሱ ፡ በዓይኔ ፡ አየሁህ (፪x) አቤት ፡ ጌታዬ ፡ ምስኪኑን ፡ ሲረዳ አቤት ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲደርስ ፡ ለተጐዳ አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ምስኪኑን ፡ ሲረዳ አየሁ ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲደርስ ፡ ለተጐዳ እርሱንማ ፡ በእውነት ፡ ለሚጠሩ የቅርብ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ የሩቅ ጌታንማ ፡ በእምነት ፡ ለሚጠሩ የቅርብ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ የሩቅ (፪x) ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) እርካታዬ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x) ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) ተድላዬ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x) በጉባኤ ፡ መሃል ፡ ስትከብር ፡ እያየሁ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ ሕዝብህ ፡ ሲያደንቅህ ፡ እያየሁ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ አምሮብህ ፡ ተውበህ ፡ እያየሁ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) ሹመቴ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x) ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) ድምቀቴ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x) ችግረኛ ፡ ሲጮህ ፡ ሰምተህ ፡ ዝም ፡ አትልም (፪x) የምስኪኑን ፡ ውድቀት ፡ አይተህ ፡ እንዳላየህ ፡ አትሆንም (፪x) እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ሁሉን ፡ ትረዳለህ (፪x) አደራረግህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x) አቤት ፡ ጌታዬ ፡ ምስኪኑን ፡ ሲረዳ አቤት ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲደርስ ፡ ለተጐዳ አየሁ ፡ ጌታዬን ፡ ምስኪኑን ፡ ሲረዳ አየሁ ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲደርስ ፡ ለተጐዳ እርሱንማ ፡ በእውነት ፡ ለሚጠሩ የቅርብ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ የሩቅ ጌታንማ ፡ በእምነት ፡ ለሚጠሩ የቅርብ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ የሩቅ (፪x) ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) እርካታዬ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x) ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) ተድላዬ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x) መቃብር ፡ ተከፍቶ ፡ እያየሁ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ ድንጋይ ፡ ተንከባሎ ፡ እያየሁ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ ዲያቢሎስ ፡ ሲረገጥ ፡ እያየሁ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) ሹመቴ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x) ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) ድንቀቴ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.