Loading
ሥምህን ፡ ስጠራ ፡ በከንፈሮቼ ደጋግመው ፡ ይለኛል ፡ መላው ፡ እኔነቴ እስቲ ፡ ልደጋግመው ፡ ኢየሱሴ ፡ ብዬ በረከቴ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለነፍሴ ፡ ተድላዬ ስደጋግመውማ (፪x) ኑሮዬ ፡ ይባረካል ፡ ሰላሜ ፡ ይበዛልኛል ኑሮዬ ፡ ይባረካል ፡ ደስታዬ ፡ ይበዛልኛል እወድሃለሁ ፡ ስልህ ፡ ከልቤ ፡ እንደሆነ አንተው ፡ ታውቀዋለህ (፪x) እራስህ ፡ ታውቀዋለህ (፪x) እከተላለው ፡ ስልህ ፡ ወስኜ ፡ እንደሆነ ልቤን ፡ ታውቀዋለህ ፡ (፪x) ውስጤንም ፡ ታውቀዋለህ (፪x) የማይጠገብ ፡ ጣዕም ፡ የማያልቅ ፡ መዓዛዉ ፍጥረት ፡ ተደነቀ ፡ ጌታዬን ፡ ስጠራዉ እኔም ፡ አላረፍኩ ፡ አበዛሁ ፡ መጥራትን ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኦሆ ፡ አዳኝ ፡ ነው ፡ ማለት ስደጋግመውማ (፪x) ደረቁ ፡ ይለመልማል ፡ አበባው ፡ ፍሬን ፡ ይሰጣል ደረቁ ፡ ይለመልማል ፡ ቡቃያው ፡ ይሰጣል እወድሃለሁ ፡ ስልህ ፡ ከልቤ ፡ እንደሆነ አንተው ፡ ታውቀዋለህ (፪x) እራስህ ፡ ታውቀዋለህ (፪x) እከተላለው ፡ ስልህ ፡ ወስኜ ፡ እንደሆነ ልቤን ፡ ታውቀዋለህ (፪x) ውስጤንም ፡ ታውቀዋለህ (፪x) በጠዋት ፡ በማታ ፡ ስሙን ፡ ሳነሳሳው ለእኔ ፡ ድል ፡ ሆነኝ ፡ ለጠላት ፡ አበሳ ኢየሱስ ፡ ስልበት ፡ ጠላት ፡ ተሸበረ መንግስቱ ፡ ፈረሰ ፡ ወጥመድ ፡ ተሰበረ ስደጋግመውማ (፪x) ጠላቴ ፡ ይዋረዳል ፡ ሽንፈቱን ፡ ይከናንባል ጠላቴ ፡ ይዋረዳል ፡ ምርኮዬን ፡ ይመልሰዋል እወድሃለሁ ፡ ስልህ ፡ ከልቤ ፡ እንደሆነ አንተው ፡ ታውቀዋለህ (፪x) እራስህ ፡ ታውቀዋለህ (፪x) እከተላለው ፡ ስልህ ፡ ወስኜ ፡ እንደሆነ ልቤን ፡ ታውቀዋለህ (፪x) ውስጤንም ፡ ታውቀዋለህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.