Loading
የፈሰሰ ፡ ውኃ ፡ በቃ ፡ አይታፈስም ዳግመኛ ፡ ሊጠቅም ፡ እድልም ፡ የለውም ሰው ፡ ተስፋ ፡ ሲቆርጥ ፡ እንዲህ ፡ ይተርታል የሞተው ፡ ሊቀብር ፡ አልቅሶ ፡ ይወጣል ጌታ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የፈሰሰም ፡ ውኃ ዳግም ፡ ይታፈሳል ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሞቷል ፡ የተባለ ፡ በሕይወት ፡ ይኖራል ጌታ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ አይቻልም ፡ ሚባል ፡ ቃል ፡ ከቶ ፡ አይገኝም ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የወደቀ ፡ ይነሳል ፡ ተቆርጦ ፡ አይጣልም አምላኬ ፡ ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ አምላኬ ፡ ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ (ኢየሱስ) ፡ ተስፋ ፡ በጠፋበት ፣ (ኢየሱስ) ፡ ተስፋ ፡ ትሆናለህ (ኢየሱስ) ፡ ታሪክን ፡ በታሪክ ፣ (ኢየሱስ) ፡ ትለዋውጣለህ (ኢየሱስ) ፡ የጠበቁህ ፡ አያፍሩም ፣ (ኢየሱስ) ፡ በጽናት ፡ የቆዩ (ኢየሱስ) ፡ በረሃው ፡ ለምልሞ ፣ (ኢየሱስ) ፡ አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ አዩ አምላኬ ፡ ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ አምላኬ ፡ ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ ሞት ፡ ጥላውን ፡ አቅልጦ___፡ ፍርሃት ፡ ሲነግስ እምነትን ፡ ሊናጠቅ ፡ ጠላት ፡ ሲገሰግስ የሕይወት ፡ ምዕራፎች ፡ ትግላቸው ፡ በርትቶ ተስፋ ፡ ያደረጉት ፡ ሳይገኝ ፡ ዘግይቶ (ጌታ ፡ ያኔማ) ፡ ድንገት ፡ ዘምበል ፡ ስትል ፡ ሁሉም ፡ ይለወጣል (ኢየሱስ ፡ ያኔማ) ፡ የተመሳቀለው ፡ በቃልህ ፡ ይሰናዳል (ጌታ ፡ ያኔማ) ፡ ዘመን ፡ ስታመጣ ፡ እስከመቼ ፡ ላሉ (ኢየሱስ ፡ ያኔማ) ፡ በምሥጋና ፡ ሆነው ፡ ታስበናል ፡ ላሉ ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.