Loading
ክረምት ፡ አለፈ ፡ ጐርፎ ፡ አልፎ ፡ ሄደ በለስ ፡ ጐመራ ፡ ወይኑም ፡ አበበ ዘመን ፡ ተሰማ ፡ ለፍጥረት ፡ ሁሉ ምህረቱ ፡ በዝቷል ፡ እስቲ ፡ እልል ፡ በሉ አዝ፦ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ዘመን ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ለእኔማ የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ (፪x) ከቅጥሬ ፡ ኋላ ፡ እርሱ ፡ ቆሞልኝ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ጉልበት ፡ ሆኖልኝ እንዲህ ፡ ያደረገ ፡ ያ ፡ መድሃኒቴ ዘመን ፡ ማጣልን ፡ ሰምቶ ፡ ጩኸቴን(፪x) አዝ፦ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ዘመን ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ለእኔማ የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ (፪x) የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ ፡ የዕልልታዬ (፬x) መንጊያውን ፡ ስከተል ፡ ከኋላ ፡ ኋላ ምኞቴ ፡ ሃሳቤ ፡ ነበረ ፡ ሌላ ፍቅሩ ፡ ወደቀ ፡ ከእረኛው ፡ ላይ ንጉሥ ፡ አደረገኝ ፡ የለበት ፡ ከልካይ አዝ፦ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ዘመን ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ለእኔማ የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ (፪x) ከቅጥሬ ፡ ኋላ ፡ እርሱ ፡ ቆሞልኝ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ጉልበት ፡ ሆኖልኝ እዘምራለሁ ፡ ሆኜ ፡ አለቱ ፡ ላይ የዝማሬ ፡ ድምጽ ፡ ይግባልኝ ፡ ሰማይ(፪x) አዝ፦ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ዘመን ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ለእኔማ የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ (፪x) የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ ፡ የዕልልታዬ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.