Loading
በምድረ ፡ በዳ ፡ በጭንቁ ፡ ወራት በልጠህ ፡ አገኘህ ፡ ከእናትም ፡ ከአባት ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ በአመታቶችህ ዛሬም ፡ ልበልህ ፡ ይልጅነቴ አዝ፦ የልጅነቴ ፡ አምላክ ፡ የልጅነቴ የልጅነቴ ፡ ወዳጅ ፡ የልጅነቴ አንተው ፡ ነህ ፡ መድሃኒቴ በአጠገቤ ፡ ቆመህ ፡ ያበረታኽኝ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህልኝ (፪x) ሲርበኝ ፡ አብልተህ ፡ ሲጠማኝ ፡ አርክተህ እዚህ ፡ አደረስከኝ ፡ ወግ ፡ ማረግ ፡ የሆነኝ ፣ ወግ ፡ ማረግ ፡ የሆነኝ በአጠገቤ ፡ ቆመህ ፡ ያበረታኽኝ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህልኝ (፪x) የጠላቶቼን ፡ ቀስት ፡ ሰብረህ ፡ ጥለህልኝ በድካሜም ፡ ቢሆን ፡ ብርታት ፡ ሆነህልኝ ያን ፡ ሁላ ፡ አልፊአያለሁ ፡ በአንተ ፡ መድሃኒቴ ዛሬም ፡ ልበልህ ፡ የልጅነቴ የልጅነቴ ፡ አምላክ ፡ የልጅነቴ የልጅነቴ ፡ ወዳጅ ፡ የልጅነቴ አንተው ፡ ነህ ፡ መድሃኒቴ በአጠገቤ ፡ ቆመህ ፡ ያበረታኽኝ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህልኝ (፪x) አይቼ ፡ እንዳልፈራ ፡ ሰምቼ ፡ እንዳልሰጋ ተጠነከክልኝ ፡ ሆነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፣ ሆነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በአጠገቤ ፡ ቆመህ ፡ ያበረታኽኝ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህልኝ (፪x) ስወድቅ ፡ አንስተህ ፡ ስጠፋ ፡ ፈልገህ አዳፋዬን ፡ ልብሴን ፡ በደምህ ፡ አንጽተህ ፣ በደምህ ፡ አንጽተህ በአጠገቤ ፡ ቆመህ ፡ ያበረታኽኝ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህልኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.