Loading
አዝ፦ አልቅበዘበዝም ፡ ከእንግዲህማ በሥጋ ፡ አልወጣም ፡ ከእንግዲህማ ግን ፡ በቃልህ ፡ መረቤን/ነገሬን ፡ እጥላለሁ የተሻለ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ አገኛለሁ (፪x) እንደ ፡ ቃልህ ፡ መረቤን ፡ እጥላለሁ የተሻለ ፡ በቃልህ/በጌታ ፡ አገኛለሁ (፪x) የድካም ፡ ሌሊት ፡ ሆኖ ፡ ሌሊቱ ለካ ፡ ይፈተናል ፡ ሰውም ፡ ትዕግሥቱ የራሴን ፡ ጥረት ፡ ሁሉ ፡ ጥሬያለሁ ታንኳ ፡ መረቤ ፡ ባየው ፡ ባዶ ፡ ነው አሁንማ ፡ በቃልህ ፡ መረቤን ፡ እጥላለሁ አሁንም ፡ ሙግቴን ፡ ሁሉ ፡ እተዋለሁ አሁንማ ፡ የአንተ ፡ ሃሳብ ፡ ይሻላል ፡ እላለሁ አሁንማ ፡ አየሁት ፡ የእኔማ ፡ ከንቱ ፡ ነው መቼ ፡ ከጉድጓድ ፡ ጋር ፡ የይሳቅ ፡ ነገሩ የአምላኩ ፡ ቃልኪዳን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ በስጥና ፡ በኤሴቅ ፡ ሲያጋፉት ፡ ቢያያቸው ርሆቦት ፡ ደረሰ ፡ ሁሉን ፡ ትቶላቸው በረከቴ ፡ ብለው ፡ ጉድጓዱን ፡ ለሚያዩ አይደለም ፡ አልኳቸው ፡ ከላይ ፡ ነው ፡ ጉዳዩ ሰው ፡ ቆፍሮ ፡ ያመጣው ፡ ይነቅፋል ፡ ይደርቃል በቃልህ ፡ የጀመረ ፡ እርሱ ፡ መቼ ፡ ያፍራል አዝ፦ አልቅበዘበዝም ፡ ከእንግዲህማ በሥጋ ፡ አልወጣም ፡ ከእንግዲህማ ግን ፡ በቃልህ ፡ መረቤን/ነገሬን ፡ እጥላለሁ የተሻለ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ አገኛለሁ (፪x) እንደ ፡ ቃልህ ፡ መረቤን ፡ እጥላለሁ የተሻለ ፡ በቃልህ/በጌታ ፡ አገኛለሁ (፪x) ስለ ፡ እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ሃሳቢ ፡ አልሻም ውጥኔ ፡ በእጄ ፡ አለው ፡ መድረሻ ብዬ ፡ ፎክሬ ፡ በራሴ ፡ ትግል ኋላ ፡ ነቃሁኝ ፡ ስደክም ፡ ስዝል አሁንማ ፡ ፈቃድህ ፡ ይሆን ፡ እላለሁ አሁንማ ፡ ከአንተ ፡ የሆነውን ፡ እሻለሁ አሁንማ ፡ . (1) . ፡ መስገን ፡ እንዳይሆን ፡ እጣዬ አሁንማ ፡ እንደቃልህ ፡ መረብ ፡ ኑሮዬ አዝ፦ አልቅበዘበዝም ፡ ከእንግዲህማ በሥጋ ፡ አልወጣም ፡ ከእንግዲህማ ግን ፡ በቃልህ ፡ መረቤን/ነገሬን ፡ እጥላለሁ የተሻለ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ አገኛለሁ (፪x) መቼ ፡ ከጉድጓድ ፡ ጋር ፡ የይሳቅ ፡ ነገሩ የአምላኩ ፡ ቃልኪዳን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ በስጥና ፡ በኤሴቅ ፡ ሲያጋፉት ፡ ቢያያቸው ርሆቦት ፡ ደረሰ ፡ ሁሉን ፡ ትቶላቸው በረከቴ ፡ ብለው ፡ ጉድጓዱን ፡ ለሚያዩ አይደለም ፡ አልኳቸው ፡ ከላይ ፡ ነው ፡ ጉዳዩ ሰው ፡ ቆፍሮ ፡ ያመጣው ፡ ይነቅፋል ፡ ይደርቃል በቃልህ ፡ የጀመረ ፡ እርሱ ፡ መቼ ፡ ያፍራል
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.