Loading
አዝ፦ ጉድለቴን ፡ ሸፍነህ ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ ያን ፡ ሁሉ ፡ ሸለቆ ፡ አዝለህ ፡ ያሻገርከኝ ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፪x) አባብዬ ፡ ተባረክልኝ (፪x) ማዳን ፡ በማይችሉት ፡ እኔስ ፡ አልመካም አንተ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ አንተ ፡ ነህ (፪x) ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ጌታ አንተ ፡ ነህ (፪x) ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ጌታ አንተ ፡ እኮ ፡ ጌታ (፪x) ፤ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ (፪x) ከንጉሥ ፡ ገበታ ፡ የማይገባኝን (፪x) ሁሉ ፡ በድካሜ ፡ የተጸየፈኝን (፪x) ከማዕድን ፡ መሃል ፡ አስቀምጠኸኛል (፪x) ኦ ፡ ኢየሱሴ ፡ ፍቅርህ ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ አድርጐኛል ፤ ምን ፡ ብል ፡ ያረካኛል ተባረክልኝ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ተባረክልኝ ከፍ ፡ በልልኝ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ አዝ፦ ጉድለቴን ፡ ሸፍነህ ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ ያን ፡ ሁሉ ፡ ሸለቆ ፡ አዝለህ ፡ ያሻገርከኝ ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፪x) አባብዬ ፡ ተባረክልኝ (፪x) ተራራ ፡ ስወጣ ፡ ጉልበት ፡ እየሆንከኝ (፪x) ስወድቅ ፡ ስነሳ ፡ እየደጋገፍከኝ (፪x) አቤት ፡ በአንተ ፡ ብርታት ፡ ስንቱን ፡ አልፌያለሁ (፪x) በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ ፤ ዛሬ ፡ ደርሻለሁ ተባረክልኝ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ተባረክልኝ ከፍ ፡ በልልኝ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ ትላንትን ፡ አልፌ ፡ እዚህ ፡ እኮ ፡ መድረሴ በአንተ ፡ ብርታት ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ በራሴ (፪x) ትላንትን ፡ አልፌ ፡ እዚህ ፡ እኮ ፡ መድረሴ በአንተ ፡ ብርታት ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ በራሴ (፪x) አይደለም ፡ በራሴ ፡ በራሴ ፡ አይደለም ፡ በራሴ (፪x) አዝ፦ ጉድለቴን ፡ ሸፍነህ ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ ያን ፡ ሁሉ ፡ ሸለቆ ፡ አዝለህ ፡ ያሻገርከኝ ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፪x) አባብዬ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.