Loading
ለእግዚአብሔር ፡ የሚሳነው ፡ አለ ፡ ወይ የሚያቅተው ፡ አለ ፡ ወይ አለ ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አለ ፡ ወይ ለኢየሱስ ፡ የሚሳነው ፡ አለ ፡ ወይ የሚያቅተው ፡ አለ ፡ ወይ አለ ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አለ ፡ ወይ በፍፁም ፡ የለም ፡ አልሰማሁም ከትላንት ፡ ዛሬም ፡ አላየሁም እኔ ፡ የገባኝ ፡ አንድ ፡ እውነት የእግዚአብሔር ፡ ታላቅነት ይሰራል ፡ ዛሬም ፡ ይሰራል ለሚያምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል አምናለሁ ፡ እኔ ፡ አይቻለሁ ለአባቴ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው (፪x) ለእግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ለእግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ለአባቴ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ለጌታ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው አበቃ ፡ ከእንግዲህ ፡ ለተባለ ፡ ሁሉ ሲያኖር ፡ አይቻለሁ ፡ በሕይወት ፡ እንደቃሉ መቃብር ፡ ከፍቶ ፡ የሞተን ፡ ያስነሳል እኔ ፡ የማመልከው ፡ አምላኬ ፡ ይሰራል አምላኬ ፡ ይሰራል ፡ አምላኬ ፡ ይሰራል አባቴ ፡ ይሰራል ፡ አባቴ ፡ ይሰራል ይሰራል ፡ ዛሬም ፡ ይሰራል ለሚያምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል አምናለሁ ፡ እኔ ፡ አይቻለሁ ለአባቴ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ለእግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ለእግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ለአባቴ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ለጌታ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ነፍሴን ፡ የፈጠረ ፡ ያበጀ ፡ ሥጋዬን ሕያው ፡ ያደረገኝ ፡ ሰጥቶ ፡ እስትንፋስን ይችላል ፡ ወይ ፡ ብዬ ፡ እንዴት ፡ ልጠርጥረው እኔ ፡ ልመን ፡ እንጂ ፡ ለጌታ ፡ ቀላል ፡ ነው ለጌታ ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ለጌታ ፡ ቀላል ፡ ነው ለአባቴ ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ለኢየሱስ ፡ ቀላል ፡ ነው ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለኢየሱስ ፡ ይቻላል (፪x) ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለአባቴ ፡ ይቻላል ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለጌታ ፡ ይቻላል ለኢየሱስ ፡ ይቻላል ፡ ለኢየሱስ ፡ ይቻላል ለጌታ ፡ ይቻላል ፡ አዎ ፡ ይቻላል ይቻላል ፡ ይቻላል ፡ ኦሆ ፡ ይቻላል ፡ ይቻላል ሟርተኛው ፡ ቢያሟርት ፡ አይሁንለት ፡ ብሎ ሊያዘገይ ፡ ቢሞክር ፡ በረከቴን ፡ ታግሎ በአምላኬ ፡ ስም ፡ ሆኜ ፡ አሸንፈዋለሁ የኢየሱስ ፡ ስሙ ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው ምሽግን ፡ ለማፍረስ ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነው ነፋስ ፡ ባይታይ ፡ ደመና ጭው ፡ ያለ ፡ ቢሆን ፡ በረሃ እኔስ ፡ አባቴን ፡ አውቀዋለሁ እንደሚሰራ ፡ አምነዋለሁ አያለሁ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ጐዶሎው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ አያለሁ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ የሌለው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ አያለሁ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ፡ ጐዶሎው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ አያለሁ ፡ ተዐምር ፡ ሰርቶ ፡ የሌለው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.