Loading
ስንቱ ተነግሮ ስንቱ ይወራ ጌት ሆይ
ለኔ ያረግከው እጅግ ብዙ ነው ውለታህ
ከጭንቀት ኣውጥተህ ሰላምን ሞላኸኝ ኣብዝተህ
ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን ለስምህ
{ውለታህ ብዙ ኣንተ የሠራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔስ ላንተ ውለታ}2
ሞትም ኣፍጦ ሲመጣ በድንገት ወደ እኔ
ማንስ ነበር ጌታ ካላንት ከጎኔ
ፍፁም አትሸበር አለሁኝ ካንተ ጋ
ብለህ አወጣኸኝ ከሰይጣን መንጋጋ
መሬት በሙሉ ወደ ወረቀት ቢለወጥ
ባህር በሙሉ ወደ ቀለም ቢቀየር
ከዚያም በኋላ ብፅፍ የአንተን ውለታ
በፍፁም አልችልም ቃላት ያጥሩኛል ጌታ
ቢፃፍ አያልቅም ጌታ የአንተ ውለታ
ሥራህ ድንቅ ነው አቤት የማትረታ
ምትጠብቀን አምላክ ከቶ የማታንቀላፋው
ልጅህን ጠብቀህ ለክብርህ አቆምከው
ብርታትና ኃይልን ፀጋንም አብዝተህልኝ
ጉልበት መጠለያ መከታ ጋሻ ሆነኸኝ
ከእሳት አውጥተህ ክብርህን በኔ የገለፅከው
ለውለታህ መልሴ እንዲያው ተመስገን ብቻ ነውComments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.