Loading
ኢየሱስ ፡ የግል ፡ ነው ፡ የግል ፡ ነው ኢየሱስ ፡ የግሌ ፡ ነው ፡ አየደል ፡ የጋራ አልናጠቀውም ፡ ከማንም ፡ ጋራ ኢየሱስ ፡ የግል ፡ ነው ፡ የግል ፡ ነው ኢየሱስ ፡ የግልሌ ፡ ነው ፡ አየደል ፡ የጋራ አልደራደርም ፡ ከማንም ፡ ጋራ አዝ፦ ዋናዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላው ፡ ሁሉ ፡ ትርፍ ፡ ነው ዋናዬን ፡ አላስነካም ፡ ካለ ፡ እሱ ፡ ትርፍም ፡ የለም (፪x) በኢየሱስ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የማገኘው ፡ ይቅርብኝ በጌታ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የማገኘው ፡ ይቅርብኝ (፪x) ጠላቴ ፡ ሊያጓጓኝ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ቢያሳየኝ ብኩርናዬን ፡ አልሽጥም ፡ የምስር ፡ ወጥ ፡ ይቅርብኝ ከዔሳው ፡ ተምሬያለሁ ፡ ለምንም ፡ ሆኛለሁኝ ጠላቴ ፡ ሊያጓጓኝ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ቢያሳየኝ ኢየሱስ ፡ አልሽጥም ፡ ሰላሳ ፡ ብር ፡ ይቅርብኝ ከይሁዳ ፡ ተምርያለሁ ፡ ለምንም ፡ ሆኛለሁኝ አዝ፦ ዋናዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላው ፡ ሁሉ ፡ ትርፍ ፡ ነው ዋናዬን ፡ አላስነካም ፡ ካለ ፡ እሱ ፡ ትርፍም ፡ የለም ዋናዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መኖር ፡ እንኳን ፡ ትርፍ ፡ ነው ዋናዬን ፡ አላስነካም ፡ ካለ ፡ እሱ ፡ መኖር ፡ የለም በኢየሱስ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የማገኘው ፡ ይቅርብኝ በጌታ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የማገኘው ፡ ይቅርብኝ በኢየሱስ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የሚሰጡኝ ፡ ይቅርብኝ በጌታ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የሚሰጡኝ ፡ ይቅርብኝ እሳቱ ፡ እጥፍ ፡ ቢነድም ፡ ለምስሉ ፡ አልሰግድም እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ አምኜው ፡ ነው ፡ ብሞትም ሊገለጥ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ሳስተያየው ፡ አይቆጭም ለምን ፡ አንደመረጠኝ ፡ ይህንን ፡ አሰምራለሁ ከሁሉም ፡ አስቀድሜ ፡ ጥሪዬን ፡ አከብራለሁ የእምነት ፡ አባቶቼን ፡ ያለፉትን ፡ እያየሁ እርሱን ፡ ለማክበር ፡ ለርሱ ፡ ለመኖር እሽቀዳደማለሁ ፡ እሽቀዳደማለሁ (፫x) እሽቀዳደማለሁ ፡ እሽቀዳደማለሁ ከእንግዲህ ፡ እልደለል ፡ ለጊዜያዊ ፡ ነገር እግዚአብሔር ፡ ያሰበልኝ ፡ የዘላለም ፡ ቁም ፡ ነገር ከዚህ ፡ አይበልጥብኝም ፡ የቀረው ፡ ሁሉ ፡ ቢቀር አወዳድሬ ፡ ይሻለኛል ፡ ብዬ ፡ እንዳልናገር የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ከምንም ፡ ጋር ፡ አይወዳደር አስተያይቼ ፡ ይሻለኛል ፡ ብዬ ፡ እንዳልናገር የእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከነጭራሹ ፡ አይወዳደር ጭክን ፡ አድርጌ ፡ ቆርቻለሁ ፡ ለኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ እኖራለሁ አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ ጠላቴ ፡ መለከት ፡ ቢነፋ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.