Loading
ትኩር ፡ ብዬ ፡ ትክ ፡ ብዬ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ (፪x) አይሃለሁ (፪x) እዛ ፡ ጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ (፬x) ግራ ፡ ገብቶኝ ፡ ሲጨንቀኝ ፡ ሲጠበኝ ኑሮ ፡ ትክት ፡ ሲለኝ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ መሄድ ፡ አቅቶኝ ፡ ስወድቅ ፡ ስነሳ ጉልበቴም ፡ ሲላላ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ ዓይኖቼን ፡ ቀና ፡ አርጌ ፡ ያልከኝን ፡ አስታውሳለሁ መከራዬንም ፡ ሃዘኔንም ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ እረሳዋለሁ (፪x) እዛ ፡ ጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ (፬x) መድኃኒቴ ፡ የልቤ ፡ ወዳጅ አንተ ፡ አትጥልምና ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ አንዴ ፡ መለስ ፡ አንዴ ፡ ደግሞ ፡ ዞር አያውቅህምና ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ ደመና ፡ አይቼ ፡ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ ክበር ፡ የምልህ በተስፋዬ ፡ ላይ ፡ ቆማለሁ ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ አይሃለሁ (፪x) እዛ ፡ ጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.