Loading
ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ልዩ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) ምን ፡ ትሰራለህስ ፡ ማነው ፡ የሚለው (፪x) ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ልዩ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) ምን ፡ ታደርጋለህስ ፡ ማነው ፡ የሚለው (፪x) እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ትልቅ የሚሰራውን ፡ የሚያውቅ አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ የሚያደርገውን ፡ የሚያውቅ ለእኔም ፡ እርሱ ፡ ካለልኝ ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁኝ ለእኔም ፡ እርሱ ፡ ካለልኝ ፡ ለምን ፡ አስባለሁ ለእኔም ፡ እርሱ ፡ ካለልኝ ፡ ማመስገን ፡ ነው ፡ ያለብኝ ማንም ፡ ከርሱ ፡ ጋራ ፡ ቢሟገትም ከሺህ ፡ ነገር ፡ እንዱን ፡ አይመልስም እንዲህና ፡ እንደዚያ ፡ ማን ፡ ይለዋል አደራረጉ ፡ ግን ፡ አፍ ፡ ያስይዛል እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ትልቅ የሚሰራውን ፡ የሚያውቅ አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ የሚያደርገውን ፡ የሚያውቅ ማንንም ፡ አይፈልግ ፡ አስተማሪ ሁልን ፡ የሚያደርገው ፡ ያላማካሪ ብቻውን ፡ ተዓምር ፡ ድንቅ ፡ ይሰራል በዛ ፡ ሲጠበቅ ፡ በዚህ ፡ ይመጣል አማካሪ ፡ የሌለው ፡ ንጉሥ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ አስተማሪ ፡ የሌለው ፡ መሪ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x) ይሄኛው ፡ ልክ ፡ አይደለም ፡ አስተካክለው ፡ ይህንን ፡ አይባልም እኔ ፡ አሳይሃለሁ ፡ በዚህ ፡ መንገድ ፡ ሂድልኝ ፡ አይባልም (፪x) አይባልም (፬x) እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ትልቅ የሚሰራውን ፡ የሚያውቅ አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ የሚያደርገውን ፡ የሚያውቅ ምድርን ፡ አደራ ፡ የሰጠው ፡ ማነው ዓለምን ፡ ያዝልኝ ፡ ያለው ፡ ማነው አገዛዝን ፡ ያስተማረው ፡ ማነው (፪x) ሁሉ ፡ የርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ አይደል ፡ ወይ የለበትም ፡ አስተዳዳሪ ፡ የበላይ (፪x) አማካሪ ፡ የሌለው ፡ ንጉሥ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ አስተማሪ ፡ የሌለው ፡ መሪ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.