Loading
አልዋሽህም ፡ ልቤን ፡ ታያለህና አልዋሽህም ፡ የልብ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ እላለሁ እርቦኛል ፡ በእውነት ፡ ፊትህ ፡ መፍሰስ ላምልክህ ፡ ይርዳኝና ፡ መንፈስህ ከስሬ ፡ ደርቼ ፡ ድሪቶዬን ከላይ ፡ ምለብሰው ፡ የፀዳውን ሰው ፡ እንደው ፡ የሚያየው ፡ ፊቴ ፡ ፊቴን እከልላለሁ ፡ ገበናዬን (፪x) ግን ፡ አንተ ፡ አትዋሽም ፡ አትታለል ዓይንህ ፡ ዘልቆ ፡ ልብን ፡ ያያል ዓይንህ ፡ ዘልቆ ፡ ልብን ፡ ያያል (፪x) የቀድሞውን ፡ ፍቅር ፡ አጣሁት ፡ ፈላልጌ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁኝ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ማደጌ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁኝ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ፡ ማደጌ የእግዚአብሔርን ፡ ደጅ ፡ እንዳልጠናሁኝ ዛሬማ ፡ ላፍታ ፡ እንኳ ፡ አቅም ፡ አጣሁ (፪x) ናፈቀኝ ፡ የጥንቱ ፡ ክብር ናፈቀኝ ፡ ቤቴ ፡ የነበረ ናፈቀኝ ፡ ኦ ፡ እግዚአብሔር ናፈቀኝ ፡ ረሃቤ ፡ ትጋቴ ናፈቀኝ ፡ ትንሿ ፡ ጐጆዬ ናፈቀኝ ፡ ያ ፡ ፀሎቴ የተገለጠው ፡ ማንነቴ ይኸው ፡ በፊትህ ፡ መድኃኒቴ አቅም ፡ አጣሁኝ ፡ አግዘኝ ያዘኝ ፡ ኃይልህን ፡ አልብሰኝ (፪x) ለአንተ ፡ ያለኝ ፡ ፍቅር ፡ ትኩስ ፡ የማይበርድ በልቤ ፡ የሚኖር ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ የሚነድ (፪x) መስሎኝ ፡ እንዳልነበር ፡ በልጅነቴ ፡ ወራት ራሴን ፡ አገኘሁት ፡ ልምድ ፡ ሆኖብኝ ፡ ቀላት ቤቴን ፡ አዘረፍኩት ፡ ከፍቼ ፡ ለጠላት ናፈቀኝ ፡ ለቃልህ ፡ ያለኝ ፡ ቦታ ናፈቀኝ ፡ ያንን ፡ የእሺታ ናፈቀኝ ፡ ኦ ፡ እርዳኝ ፡ ጌታ ናፈቀኝ ፡ ለአንተ ፡ ያለኝ ፡ ክብር ናፈቀኝ ፡ ሥምህ ፡ ሲነገር ናፈቀኝ ፡ ኦ ፡ እግዚአብሔር የተገለጠው ፡ ማንነቴ ይኸው ፡ በፊትህ ፡ መድኃኒቴ አቅም ፡ አጣሁኝ ፡ አግዘኝ ያዘኝ ፡ ኃይልህን ፡ አልብሰኝ (፪x) ይቅር ፡ ይቅር ፡ ይቅርብኝ ፡ ልመልስ ወደ ፡ ልብህ ፡ ወደ ፡ ሀሳብህ ፡ ልድረስ ልሸከመው ፡ የመስቀልህን ፡ ፍቅር ተመልሼ ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ እንዳልቀር አድስልኝ ፡ የቀድሞውን ፡ ዘመን ናፍቆት ፡ ሆኖ ፡ ምኞት ፡ ሆኖ ፡ እንዳይቀር ሰምቼ ፡ አንተን ፡ እንዳፈራበት ለም ፡ አድርገው ፡ የልቤን ፡ መሬት (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.