Loading
አንድ ሁለት ቢለው ያ ክፉ በምክሩ ዘው ብሎ ገባ ቢቀለዉ ነገሩ ዛሬ ነገን ሲወልድ ቀኑን ቀን ሲገፋ እዛው ቀጠለበት ልክ እንዳለው ተስፋ እያዩ አያዩ×2 እየሰሙ አይ የልቦና አይን ካልበራ እኮ ከላይ ይኸው ተቀምጧል አለ በእምነት ቤት መቅረዙ ግን ጠፍቷል የለዉም ዘይት ማሰብ አይፈልግም ቃሉን በእዉነቱ ከንቱ መመላለስ ይኸው ነው እምነቱ እግሩ በእምነት ቤት ቤተኛ ልቡ ግን ዉጭ ነው አለመኛ ×2 እያሳሳቀች አለም እያባበለች አለም ጣፋጭ ፍሬዋን አለም እያቀመሰች አለም ኋላ ግን ኋላ አለም ትተፋሀለች አለም እንዳትሽር አርጋ አለም ትጥልሀለች አለም ተለይ ×3 እልፍ በል ተለይ×6 የአምላክህን እቃ የምትሸከም ሆይ እንድትኖርባት ነው አለምን የሰራት በእርሷ ዉጣ ግባ ተመላለስባት እንጂ አትጠላለፍ በክፉ ነገር የእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የቄሣር ለቄሣር ያቃተህን ንገረው ጌታ ቸር ወዳጅ ነው ስትበረታ ብቻ አይደል የኔ ነህ የሚለው በትህትናና በተዋረደ በመንፈስ ሆነህ እንዲህ በል በለሲቱን አትቁረጣት አንድ አመት ታገሳት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.