Loading
በማዘን ፡ መተከዝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይከብር ፡ ይመስል ምንድን ፡ ነው ፡ መርበትበት ፡ ሁልጊዜ ፡ መቆዘም ጠላት ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ በዚያ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ የሚለው ምን ፡ ይጨምራል ፡ የአምላክን ፡ ሃይል ፡ መጠርጠር ፡ ነው አዝ፦ አላንጐራጉርም ፡ አንገቴንም ፡ አልደፋም እግዚአብሔር ፡ እንቅቶኛል ፡ ጊዜዬን ፡ አላጠፋም (፪x) ምን ፡ አሸማቀቀኝ ፡ ምን ፡ አንገቴን ፡ አስደፋኝ ጌታዬ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆኖ ፡ እያየሁኝ የማልፍበት ፡ ሁሉ ፡ እንደምናምን ፡ ቢመስልም ነጥሬ ፡ እወጣለሁ ፡ ወደኋላዬ ፡ አልልም አዝ፦ አላንጐራጉርም ፡ አንገቴንም ፡ አልደፋም እግዚአብሔር ፡ እንቅቶኛል ፡ ጊዜዬን ፡ አላጠፋም (፪x) የትም ፡ ስፍራ ፡ ብሆን ፡ የሚይዘኝ ፡ ምንም ፡ የለም እሰራለሁ ፡ ስራ ፡ አለኝ ፡ ገና ፡ ያልጀመርኩት ሲያየኝ ፡ ጠላቴ ፡ ለዐይኑ ፡ ባልሞላለትም እግሬ ፡ የረገጠበት ፡ ሰላም ፡ አልሰጠውም አዝ፦ አላንጐራጉርም ፡ አንገቴንም ፡ አልደፋም እግዚአብሔር ፡ እንቅቶኛል ፡ ጊዜዬን ፡ አላጠፋም (፪x) የደከምኩ ፡ ስመስለው ፡ አሳድደዋለሁ ተኛታለች ፡ ብሎ ፡ ሲል ፡ ህልምን ፡ አልማለሁ ዛሬ ፡ አዘነች ፡ ሲል ፡ እዘምራለሁ ከአምላኬ ፡ ተጣብቄ ፡ ግራ ፡ አጋባዋለሁ አዝ፦ አላንጐራጉርም ፡ አንገቴንም ፡ አልደፋም እግዚአብሔር ፡ እንቅቶኛል ፡ ጊዜዬን ፡ አላጠፋም (፪x) ትልቅን ፡ ትልቅን ፡ ነገርን ፡ ሁልጊዜ አስባለሁ ፡ አምላኬ ፡ ያንኑ ፡ ሲያደርግ ፡ አየዋለሁ ከፍ ፡ ያለውን ፡ ከፍ ፡ ያለውን ፡ ነገርን ፡ ሁልጊዜ አስባለሁ ፡ አምላኬ ፡ ያንኑ ፡ ሲያደርግ ፡ አየዋለሁ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.