Loading
ዝናቡ ፡ ከላይ ፡ ሲዘንብ ጐርፉም ፡ ከታች ፡ ሲሞላ ከመሃል ፡ ቆሜ ፡ እምተርፍ ፡ አልመስል በንገዱን ፡ ባላውቀውም እርሱ ፡ ብዙ ፡ መንገድ ፡ አለው ይህ ፡ ይረዳኛል ፡ ያወጣኛል አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ አንድ ፡ ነገር ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ ብቻዬን ፡ አይደለሁም ፡ ኧረዳት ፡ አለኝ (፪x) ሓሩሩ ፡ ቢያቃጥለኝ ፊቴ ፡ ጠቁሮ ፡ ቢታይ በረሃው ፡ ቅስሜን??? ፡ ቢያደክመኝም ብቻዬን ፡ ብመስል ፡ እንኳን ብቻዬን ፡ አይደለሁም እወጣዋለሁ ፡ እረዳት ፡ አለኝ አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ አንድ ፡ ነገር ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ ብቻዬን ፡ አይደለሁም ፡ ኧረዳት ፡ አለኝ (፪x) ከጐኔ ፡ ነው ፡ ሁልጊዜ ስለእኔ ፡ ግድ ፡ ይለዋል ሃዘኔ ፡ ይሰማዋል ፡ የልቤን ፡ ያውቃል የሚያስጨንቁኝ ፡ ሁሉ በእርሱ ፡ ጉልበት ፡ ይፈታሉ ሳልነግረው ፡ ይረዳኛል ፡ የልቤን ፡ ያውቃል አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ አንድ ፡ ነገር ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ ብቻዬን ፡ አይደለሁም ፡ ኧረዳት ፡ አለኝ (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.