Loading
ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ አምልኮዬን ፡ አላቆምም (፪x) አዳዲስ ፡ መዝሙር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና ፡ (ምሥጋና ፡ ምሥጋና) ለታላቅነቱ ፡ (ምሥጋና ፡ ምሥጋና) (፪x) ታሞ ፡ አዘነ ፡ ሞቶ ፡ አለቀሰ የሰው ፡ እርዳታ ፡ መች ፡ ከዚህ ፡ አለፈ ሲታመም ፡ ቀርቶ ፡ ሞቶ ፡ ቢደርስ ሬሳ ፡ አይተናል ፡ ሲቀሰቀስ ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ አምልኮዬን ፡ አላቆምም (፪x) የቤቱን ፡ ትልቅ ፡ ኤልያብን ፡ ትቶ ቀቡልኝ ፡ ካለ ፡ እረኛውን ፡ ጠርቶ ያዕቆብን ፡ ወዶ ፡ ኤሳውን ፡ ከጠላ ሲረፍድ ፡ ይገባል ፡ የጌታ ፡ ስራ ትክክል ፡ ነው ፡ ትክክል ፡ ነው (፮x) የሰማይ ፡ መስኮት ፡ ቢከፈት ፡ እንኳን በአንድ ፡ ቀን ፡ ይሄ ፡ እንዴት ፡ ይሆናል ንጉሡ ፡ እምቢ ፡ ቢል ፡ ትንቢት ፡ አዳምጦ ሳይበላ ፡ ሞተ ፡ በሰው ፡ ተረግጦ ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ አምልኮዬን ፡ አላቆምም (፪x) አዳዲስ ፡ መዝሙር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና ፡ (ምሥጋና ፡ ምሥጋና) ለታላቅነቱ ፡ (ምሥጋና ፡ ምሥጋና) (፪x) ትክክል ፡ ነው ፡ ትክክል ፡ ነው (፮x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.