Loading
አይሁዶች ፡ ሃሳባቸው ፡ በሃማ ፡ እጅ ፡ መጥፋታቸው (፪x) ማን ፡ እንደሚሞት ፡ ላልታወቀ ፡ መስቀያው ፡ ተሰርቶ ፡ አለቀ ጆሮውን ፡ ለሰማይ ፡ ሰጥቶ ፡ የምድሩን ፡ ለሃማ ፡ ትቶ ከአባቱ ፡ ያዳመጠ ፡ ያው ፡ በክብር ፡ ተገለጠ የሰማው ፡ ከላይ ፡ ነው (፫x) የሰማው ፡ ከላይ ፡ ነው (፫x) አዝ:- ሰሞኑን ፡ ሰማሁ ፡ ክፉ ፡ ወሬ በተወለድኩበት ፡ በአገሬ ትንሹ ፡ ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ አባትዬው ፡ ሰምቶ ፡ ጉድ ፡ አለ እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም ፡ አለሁ እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም (፫x) ይሄ ፡ ነው ፡ ተነስ ፡ ቀባው ፡ የኔን ፡ ልብ ፡ ያሳረፈው (፪x) ነብዩ ፡ ቀብቶት ፡ ወጣ ፡ ቅባቱ ፡ ነገር ፡ አመጣ ከጐልያድ ፡ ጭንቅ፡ ያሳረፈውን ፡ መልሶ ፡ ጠላት ፡ ሆነዉ የእግዚአብሔር ፡ ቃሉ ፡ አልፈረሰም ፡ ሳኦል ፡ ሞቶ ፡ ዳዊት ፡ ነገሠ የሰማው ፡ ከላይ ፡ ነው (፫x) የሰማው ፡ ከላይ ፡ ነው (፫x) አዝ:- ሰሞኑን ፡ ሰማሁ ፡ ክፉ ፡ ወሬ በተወለድኩበት ፡ በአገሬ ትንሹ ፡ ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ አባትዬው ፡ ሰምቶ ፡ ጉድ ፡ አለ እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም ፡ አለሁ እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም (፫x) ስኬቴ ፡ ያስከፋቸው ፡ ውድቀቴ ፡ ደስ ፡ ያላቸው (፪x) ላልሞተ ፡ ሰው ፡ አስለቅሶ ፡ በቁሜ ፡ አፈር ፡ አልብሰው ልብ ፡ ሊስቅ ፡ እንደለመዱ ፡ ለታይታ ፡ ሙሾ ፡ ወረዱ ከሰማይ ፡ በቃቹህ ፡ አለ ፡ ለዘሩት ፡ ዋጋ ፡ ከፈለ የያዘኝ ፡ እጁ ፡ ነው (፫x) የያዘኝ ፡ እጁ ፡ ነው (፫x) አዝ:- ሰሞኑን ፡ ሰማሁ ፡ ክፉ ፡ ወሬ በተወለድኩበት ፡ በአገሬ ትንሹ ፡ ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ አባትዬው ፡ ሰምቶ ፡ ጉድ ፡ አለ እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም ፡ አለሁ እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.