Loading
ፀሐይ ፡ ዘምበል ፡ ብላ ፡ አመሻሹ ፡ ላይ ፡ ነኝ ችግሬ ፡ እያለ ፡ ሚነጋ ፡ መሰለኝ ለካ ፡ አምላኬ ፡ ሰምቷል ፡ ጠላቴ ፡ እየዛተ የተዘጋጋው ፡ በር ፡ አውቆ ፡ ተከፈተ አዝ:- ሰይጣን ፡ ውሸቱን ፡ ነው (፪x) ፡ ትሞታለህ ፡ ያለው (፪x) ኢየሱስ ፡ እውነቱን ፡ ነው (፫x) ፡ አትሞትም ፡ ያለው (፪x) በሞትና ፡ በእኔ ፡ አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶ ምን ፡ ረዳኝ ፡ አትበል ፡ ከረፈደ ፡ መጥቶ አምላክህ ፡ ሲነሳ ፡ ሲያንጐዳጉድ ፡ ከላይ መከራህ ፡ በጓዳ ፡ ክብርህ ፡ በአደባባይ ይደርደር ፡ ይደርደር ፡ በገና ዕድሜ ፡ ቀጠለልኝ ፡ ይገባዋልና ሌላ ፡ ሌላ ፡ ምሥጋና (፬x) ፈሮን ፡ ከሁአላ ፡ ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊት ፡ ነው ግብጽ ፡ አይመለሱም ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ብለው በአራቱም ፡ አቅጣጫ ፡ ሞት ፡ እየቸኮለ የገዳዬ ፡ ገዳይ ፡ ከሰማይ ፡ ብቅ ፡ አለ አዝ:- ሰይጣን ፡ ውሸቱን ፡ ነው (፪x) ፡ ትሞታለህ ፡ ያለው (፪x) ኢየሱስ ፡ እውነቱን ፡ ነው (፫x) ፡ አትሞትም ፡ ያለው (፪x) ይደርደር ፡ ይደርደር ፡ በገና ዕድሜ ፡ ቀጠለልኝ ፡ ይገባዋልና ሌላ ፡ ሌላ ፡ ምሥጋና (፬x) (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.