Loading
ሰው ፡ አነሰ ፡ አይባል ፡ እከሌ ፡ ነኝ ፡ ይላል ከስሙ ፡ አስቀድሞ ፡ ያለ ፡ የሌለ ፡ ነገር ፡ ጨማምሮ ፡ ይናገራል ሥራህስ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ቢጠይቁት አሳምሮ ፡ ያወራል ፡ ያብራራል ፡ ከሰሙት ለመጥምቁ ፡ ዮሐንስ ፡ ኢሄ ፡ እድል ፡ ደረሰው አንተ ፡ ማነህ ፡ ብሎ ፡ ብዙ ፡ ህዝብ ፡ ጠየቀው እንዲህ ፡ ሲል ፡ መለሰ ፡ ስለ ፡ ማንነቱ ሳያፍር ፡ ገለጠ ፡ እውነትን ፡ ከውሸቱ እኔ ፡ ጠራጊ ፡ ነኝ ፣ ድምጽ ፡ ነኝ ፣ ምጮኸው መንገድ ፡ የማዘጋጅ ፡ ከኋላ ፡ ሄዳለሁ አይደለሁም ፡ ኤልያስ ፡ ከነብያቶች ፡ አንዱ የማመቻች ፡ ነኝ ፡ ጥርጊያ ፡ ለመንገዱ አላቸው ፡ መልሶ ፡ ራሱን ፡ አሳንሶ የጫማውን ፡ ጥፍር ፡ ልፈታ ፡ የማይገባኝ ከእርሱ ፡ አንሳለሁኝ እኔ ፡ ላንስ ፡ ይገባል ፡ እርሱ ፡ ከእኔ ፡ ይበልጣል እኔ ፡ በውኃ ፡ ሳጠምቅ ፡ በእሳት ፡ ያጠምቃል እርሱ ፡ ከእኔ ፡ ይበልጣል[1][2] እንዲህ ፡ ነው ፡ እንግዲህ ፡ ትህትና እንዲህ ፡ ነው ፡ እንግዲህ ፡ ዝቅ ፡ ማለት (፪x) ራስን ፡ ማወቅ ፡ ማንነትን ሰው ፡ መሆንን ፡ መረዳትን ያበዛዋል ፡ መዋረድን ሒሳቡ ፡ ደግሞ ፡ ኢሄ ፡ ነው ዝቅ ፡ ያለ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ የሚለው (፪x) እኔ (፮x) ፡ ባልኩኝ ፡ ቁጥር እወጣለሁኝ ፡ ካለሁበት ፡ አጥር እኔ (፮x) ፡ ያልኩኝ ፡ ለታ ያበቃልኛል ፡ የማታ ፡ የማታ እኔነቴ ፡ መድከሚያዬ እኔነቴ ፡ መውደቂያዬ እኔነቴ ፡ መወጫዬ እኔነቴ ፡ መቃብሬ ስንቱ ፡ ተቀበረ ፡ በእኔነት ፡ መቃብር ትንሳዔ ፡ ያምጣለት ፡ ትሁቱ ፡ እግዚአብሔር (፪x) እንደ ፡ እንጀራ ፡ አይለመን ፡ ትህትና መለወጥ ፡ ነዉ ፣ መወሰን ፡ ነዉ ፣ የሚያስፈልገዉ በትዕቢት ፡ ከጋሉ እኔነቴ ፡ መድከሚያዬ እኔነቴ ፡ መውደቂያዬ እኔነቴ ፡ መወጫዬ እኔነቴ ፡ መቃብሬ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.