Loading
አዝ፦ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x) የማይቀበል ፡ ጉቦ ፡ መማጸኛ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ በቅን ፡ የሚፈርድ ፡ የማይወናበድ ግራና ፡ ቀኙን ፡ አይቶ ፡ ማይዘላብድ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x) ነፃ ፡ አወጣኝ ፡ ሆኖ ፡ ጠበቃ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ከሳሼ ፡ ተነስቶ ፡ ሴራውን ፡ መስርቶ የጠቀመኝ ፡ መስሎ ፡ ጐትጉቶ ፡ ጐትጉቶ ሴራውም ፡ ተሳክቶ ፡ እኔንም ፡ አስቶ መልሶ ፡ ከሰሰኝ ፡ እንዲፈረድብኝ ከዳኛው ፡ አቆመኝ ፡ ጠበቃ ፡ ሳይኖረኝ የችሎቱም ፡ ዳኛ ፡ አባቴ ፡ ሆነና ተከስሼ ፡ ስቀርብ ፡ በልቡ ፡ አዘነና ሞታ ፡ አትቀርም ፡ እሷ ፡ ብሎ ፡ አሰበና ሞቷን ፡ እሞታለሁ ፡ ብሎ ፡ በየነልኝ በኔው ፡ ሐጥያት ፡ እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ ሞተልኝ ሞተልኝ ፡ ሞተልኝ ፡ ሞተልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ታደገኝ ሞተልኝ ፡ ሞተልኝ ፡ ሞተልኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ታደገኝ አዝ፦ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x) የማይቀበል ፡ ጉቦ ፡ መማጸኛ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ በቅን ፡ የሚፈርድ ፡ የማይወናበድ ግራና ፡ ቀኙን ፡ አይቶ ፡ የማይዘላብድ አዝ፦ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x) ነፃ ፡ አወጣኝ ፡ ሆኖ ፡ ጠበቃ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ነፍሴን ፡ እንደ ፡ ጭልፊት ፡ ሲነዳት ፡ ከፊት ፡ ፊት ወስዶ ፡ ቢከሳትም ፡ ትልቁ ፡ ዳኛ ፡ ፊት ከነአደፈው ፡ ልብሴ ፡ ተጐናጽፋ ፡ ነፍሴ ገልጦ ፡ ገበናዬን ፡ አሳይቶ ፡ ጉዴን ሊያሳጣኝ ፡ ከችሎት ፡ ያዋረደኝ ፡ መስሎት እድፋሙ ፡ ጥምጣም ፡ ቢታሰርም ፡ በጣም አዘዘ ፡ ግን ፡ ዳኛው ፡ ፍርድ ፡ እስከ ፡ ወዲያኛው ይፈታ ፡ ጥምጣሙ ፡ ኮተታ ፡ ኮተቱ እንኪ ፡ አዲሱ ፡ ልብስሽ ፡ ታዪ ፡ ተጐናጽፈሽ ወጥተሻል ፡ አርነት ፡ ሂጂ ፡ በነፃነት አርነት ፡ አርነት ፡ አርነት ፡ ሄድኩኝ ፡ በነፃነት አርነት ፡ አርነት ፡ አርነት ፡ ወጣሁ ፡ በነፃነት አዝ፦ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x) የማይቀበል ፡ ጉቦ ፡ መማጸኛ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ በቅን ፡ የሚፈርድ ፡ የማይወናበድ ግራና ፡ ቀኙን ፡ አይቶ ፡ የማይዘላብድ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፪x) ነፃ ፡ አወጣኝ ፡ ሆኖ ፡ ጠበቃ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ ፡ እውነተኛ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ዳኛ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.