Loading
በጨለማ ፡ እያለሁ ፡ ነፍሴ ፡ ተንከራትታ ፡ መቼ ፡ ተውከኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) የሰይጣን ፡ ምርኮኛ ፡ ሆኜ ፡ የተጠቃሁ ፡ አወጣኸኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) ብቻዬን ፡ ሳለቅስ ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ ስጮህ ፡ ብዬ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ ደረስክ ፡ ሳትቆይ ፡ እስከማታ ፡ ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) አዝ፦ እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል ፡ ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር ትንሽ ፡ ከቀለለኝ ፡ ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ ስላረግከው ፡ ተዓምር ፡ ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ በጠላቴ ፡ መንግስት ፡ በእቅዱ ፡ ውስጥ ፡ ሆኜ ፡ አይተኸኛል ፡ መድኃኒቴ (፪x) አወጣኸኝ ፡ ከእጁ ፡ ሳትጠፋ ፡ ሕይወቴ ፡ ክበርልኝ ፡ መድኃኒቴ (፪x) ልትጠቀምብኝ ፡ በኔ ፡ ልትሰራ ፡ ፈልገህ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) ነጥቀህ ፡ የታደግከኝ ፡ ከዚያ ፡ ባለ ፡ ጋራ ፡ ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) አዝ፦ እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል ፡ ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር ትንሽ ፡ ከቀለለኝ ፡ ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ ስላረግከው ፡ ተዓምር ፡ ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ ለኃጥዕ ፡ ለጻድቅ ፡ ፀሐይህ ፡ ይወጣል ፡ ለፍጥረትህ ፡ ሁሉ ፡ ይወጣል (፪x) ቸርነትህ ፡ ፍቅርህ ፡ መች ፡ ይበላለጣል ፡ ለሁሉም ፡ ሰው ፡ ሰጥተኸዋል (፪x) ለኔ ፡ ግን ፡ አወጣህ ፡ ብርሃን ፡ ሌላ ፡ ፀሐይ ፡ ካልጠበቅኩት ፡ አቅጣጫ ፡ ላይ (፪x) የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ወልድ ፡ ወረደ ፡ ከላይ ፡ ክበርልኝ ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x) አዝ፦ እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ ፡ ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል ፡ ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር ትንሽ ፡ ከቀለለኝ ፡ ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ ስላረግከው ፡ ተዓምር ፡ ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.